ቼልሲ ከ አርሰናል ታክቲካዊ ቅድመ ዳሰሳ


በሠላም ጎሳዬ  

በአርሰናል ቤት አልቫሮ ሞራታን መጠንቀቅ እንዳለበትና በእንግድነት ወደ ብሪጅ ሲጓዝ የሜሱት ኦዚል ጉዳት ለምን በግዙፉ ተነሳ?

በእንግሊዝ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል ቼልሲ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል:: ይህም በሳምንት ልዩነት ውስጥ ሁለት ጊዜ ብቅ ብሏል::

ባለፈው ረቡዕ በኤምሬትስ የተደረገው ጨዋታ አንዱ ነው:: እናም የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ከዚህ ጨዋታ የሚማሩት ነገር እንዳለ ግልፅ ነው::
ቀጣዩ ፅሁፍም የሁለቱ ቡድኖች ታክቲካል አቀራረብ ምን ሊመስል እንደሚችልና ቡድኖቹ በየትኛው ጎን መሻሻል እንደሚገባቸው ያስቃኘናል::
የአርሰናል የተከላካይ መስመርና ሙስታፊ በጣም ተሻሽለው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
በዚህ የውድድር ዘመን አርሰን ቬንገር በተለያዩ ጨዋታዎች በሶስት ወይም በአራት ተከላካዮች የኃላ መስመራቸውን ሲገነቡ ተስተውለዋል::
ይህም ማለት ደግሞ በተከላካዮች ዘንድ ግዳጃቸውን በተገቢው መንገድ እንዳይፈፅሙ ግርታን ፈጥሮባቸዋል:: ይህ አለመግባባት ደግሞ ከምንግዜውም በላይ ባለፈው ከቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ በጉልህ ታይቷል::
ኤምሬትስ ላይ በተደረገዉ ጨዋታ በሶት ተከላካዮች የተገነባው የአርሰናል የኃላ መስመር በመጀመሪያ 15 ደቂቃዎች ውስጥ በተደጋጋሚ ለተጋጣሚያቸው ተጋልጠዋል እንዳውም ቼልሲ የመሪነት ጎል ማስቆጠር ይጠበቅበት ነበር::
በዚያ ጨዋታ ላይ ሽኮድራን ሙስታፊ በብዙ አጋጣሚዎች ክለቡን እንደበደለ ተቆጥሮ በብዙ ተፈርዶበታል ምክንያቱም ኳሶችን በቸልተኝነት በመተውና መገኘት ባለበት ትክክለኛ ቦታ ላይ ባለመገኘቱ::
ለዚህም ይመስላል ኤደን ሃዛርድ የሙስታፊን በቦታው ያለመገኘት ስህተት በመጠቀም በተደጋጋሚ አደጋ ለመፍጠር ሲሞክር የነበረው:: ሞራታም በተመሳሳይ ሙስታፊ በቸልተኝነት የተዋቸውን ኳሶች ለመጠቀም ሞክሯል::
የእሱ በጨዋታው ላይ እንዲህ መቸገር እና ግራ መጋባት ተከላካዮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዳልተረዱ በግልፅ ያሳየ ሆኖ አልፏል:: ‘ድንጋጤ’ የጨዋታው ርዕሰ ሆኗል::
ቤለሪን የሃዛርድን እንቅስቃሴ ለመግታት በሚያደርገው የወደፊት ጉዞ ሙሉ ሀይሉን መጠቀም አለበት::
ባለፈው ሳምንት ቤለሪን የአቻነቷን ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል:: በአጠቃላይ በቀኝ መስመር ለሚደረገው እንቅስቃሴ ግዳጅ ተጥሎበት ነበር:: 
ነገር ግን ችግር የነበረው በፕሪምየር ሊጉ አሉ ከሚባሉ ድንቅ የፈጣሪነት ክህሎት ካላቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ሃዛርድን በአንፃራዊነት መግጠሙ ነው:: ሃዛርድ ከመድፈኞቹ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ ኳስን በደንብ ለመጠቀም የሚያስችሉ ቦታዎችን አግኝቶ ነበር::
በኃላ መስመር ላይ ከተሰለፉ ሶስት ተጫዋቾች የቀኝ የመሃል ተከላካዩ ይህንን ቦታ መዝጋት ነበረበት:: ነገር ግን ሃዛርድ ቀላል ተጫዋች አይደለም ምናልባትም ቤለሪን ይህንን እንቅስቃሴውን ለመግታትና ስጋቱን ለመቀነስ የነበረውን ብቃት እጥፍ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር::
በዛሬው ጨዋታ ላይ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ዲሲፕሊንድ መሆን ከስፔናዊው የሚጠበቅ ነው::
የሜሱት ኦዚል ከጨዋታው ውጪ መሆን በእጅጉ እየተሰማ ነው
ቼልሲ በዛሬው ምሽት ጨዋታ ላይ ከአርሰናል የሚደርስበትን ስጋት ለመቀነስ አንድ ነገር ብቻ በጥሩ መንገድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል-የሜሱት ኦዚልን እንቅስቃሴ መግታት እና የሚጠቀምባቸው ቦታዎችን መዝጋት::
ይህ ጀርመናዊ ከአርሰናል ጋር የሚፋታበት ጊዜ እንደደረሰ እየተነገረ ይገኛል:: ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጨዋታ ላይ አርሰናል ላደረገው የወደፊት የማጥቃት እንቅስቃሴና በተጋጣሚያቸው ላይ ለፈጠሩት ስጋት ዋነኛ ተዋናይ እንደነበር ይታወሳል::
በጨዋታው ላይ ስድስት ጊዜ ብቻ ዕድሎችን መፍጠር ሲችሉ ሶስቱ የተገኙት በኦዚል አማካኝነት ነበር::
እናም አሁን ላይ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ እንደሚሆን እየተነገረ ይገኛል ይህም ማለት ለቼልሲ ምቾት ይሰጣል::
አልቫሮ ሞራታን ተጠንቀቁት
ባለፈው ሳምንት ኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ላይ ከሚነሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች መካከል አንዱ የአልቫሮ ሞራታ በተደጋጋሚ ግልፅ የማግባት ዕድሎችን አግኝቶ ሳይጠቀምባቸው መቅረቱ ይገኝበታል::
ሶስት ጊዜ ከግብ ጠባቂው ፒተር ቼክ ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶም ነበር::ሁለት ጊዜ በቀኝ ቋሚ የወጡ ኳሶችን ሞክሯል:: በጨዋታው ላይ በመጨረሻ ደቂቃዎች ከተገኙ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች በአንዱ የሞከራት ኳስ በቀጥታ ለግብ ጠባቂው የደረሰች ሆናለች::
እንዳውም በዚህ ጨዋታ ላይ ባሳየው የአጨራረስ ድክመት ቀልዶችን አስተናግዷል:: በጭንቅላቱ እንጂ በእግሩ ኳስና መረብን ማገናኘት እንደማይችል ተሳልቀውበታል:: ነገር ግን ስህተቱን የሚደግምበት ሁኔታ ጠባብ ስለሆነ አርሰናሎች ሊጠነቀቁት ይገባል::
በዚህ የአርሰናል የተከላካይ ክፍል ደካማነትና ቸልተኛነት እነዚያን ዕድሎች ድጋሚ ቢያገኝ አይጠቀምባቸውም ማለት የዋህነት ነው:: እናም ብሪጅ ላይ ግብ ከሚያስቆጥሩ ተጫዎች የስም ዝርዝር ውስጥ እራሱን ማጣት አይፈልግም::
የማርከስ አሎንዞ የወደፊት እንቅስቅሴ…ስለዚህ ሊያዝ ይገባል
ባለፈው ሳምንት ጨዋታ ላይ አሎንዞ ግብ ማስቆጠሩ ከአጥቂው አልቫሮ ሞራታ እንደሚሻል በብዙዎች ተወድሷል:: እንደ አንድ የግራ ኃላ ተጫዋች ኳስና መረብን በተደጋጋሚ ማገናኘቱ አስገራሚ ሆኗል:: 
ኤምሬትስ ላይ ግብ ሲያስቆጥር እንደው በአጋጣሚ አልነበረም እዛ ቦታ ላይ እንዲገኝ በአንቶንዮ ኮንቴ ተገፍቶ እንጂ:: በተደጋጋሚ የአየር ላይ ኳሶች ወደ ሳጥን ውስጥ ሲሻገሩ በመጨረሻ ሶስተኛ ላይ አሎንዞን ማየት እየተለመደ መጥቷል::
በዛሬው ጨዋታ አርሰናል ትኩረት ሊያደርግባቸው ከሚገቡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይጠቀሳል::
የውድድር ዘመኑ ምርጥ አራት ጨዋታዎች በኤምሬትስ ተደርገዋል ከሌስተር ሲቲ ማን.ዩናይትድ ሊቨርፑል እና ቼልሲ::
አርሰናል እነዚህን ጨዋታዎች ሲያደርግ የተከላካዮች ቅንጅት መፋለስ በትክክል ታይቷል:: በራቸው ለተጋጣሚ ፈፅሞ ክፍት ነበር:: ባለፈው ሳምንት ብቻ ተጋጣሚያቸው 19 ጊዜ ሹት እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል:: ቼልሲ ደግሞ ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ይህንን ዕድል ካገኘ ከመጠቀም ወደኃላ አይልም:: በእርግጠኝነት ጨዋታውን የሚያደርጉት በጋለ ስሜት እና በጥልቅ ፍላጎት ስለሆነ::

1 hour ago · Sent from Web

Advertisements