የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ መራዘሙን አሳወቀ

የፊታችን ቅዳሜ ጥር አምስት በአፋር ክልል፣በሰመራ ከተማ ሊካሄድ የነበረው የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ መራዘሙን ፌዴሬሽኑ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሀን በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

በተደጋጋሚ ጊዜ ለመራዘም የበቃው በውዝግብ የታጀበው የፌዴሬሽኑ የፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ በድጋሚ ለየካቲት 24 ቀጠሮውን አድርጓል።

የካቲት 24 በእለተ ቅዳሜ በሚደረገው ምርጫው ቦታው በፊት በተያዘለት በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል።

እግርኳስ ፌዴሬሽኑ ለመገናኛ ብዙሁን ዛሬ በላከው ደብዳቤ መሰረት የምርጫ እለቱ ሊራዘም የቻለው ከፊፋ በተፃፈ ደብዳቤ ምክንያቶች እንደሆነ ይገልፃል።

ለመገናኛ ብዙሀን የተላከው ሙሉ ደብዳቤውን ከታች ይመልከቱ።

Advertisements