ኢላማ / ማንችስተር ዩናይትድ ከሳንቼዝ ጋር ግንኙነት ማድረጉን እና ለዝውውሩም አንድ ተጫዋቹን በጭማሪነት ለመስጠት እንዳሰበ ተገለፀ

ማንችስተር ዩናይትድ አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማስፈረም ከቺሊያዊው አጥቂ ጋር ድንገተኛ ግንኙነት ማድረጉንና ዝውውሩ እንዲሳካም ሄነሪክ ማኪቴሪንን የዝውውሩ አካል በማድረግ ለአርሰናል ለመስጠት ማሰቡ ተገለፀ። 

የእንግሊዙ ታማኝ የዜና ተቋም ያወጣው መረጃ እንዳመለከተው ወደ ኢትሀድ እንደሚያመራ እየተነገረ ያለውን የ 29 አመት ተጫዋች ለማጥመድ ዩናይትድ ፉክክሩን ተቀላቅሏል። 

የኦልትራፎርዱ ክለብ ቺሊያዊውን አጥቂ ለማግኘት ሲልም በክለቡ ቦታ እያጣ የመጣውን የጨዋታ አቀጣጣይ ሄነሪክ ማኪቴሪያንን የስምምነቱ አንድ አካል አድርጎ ለማቅረብ ማሰቡ ተያይዞ ተገልጿል። 

ሮሜሉ ሉካኩ፣ አንቶኒ ማርሻል፣ ማርከስ ረሽፎርድ እና ዝላታን ኢብራሂሞቪችን የያዘው የሞውሪንሆ ስብስብ ሳንቼዝን ማሰቡ ከጋብሬል ጂሰስ መጎዳት በኋላ አዲስ አጥቂ ለማምጣት አጥብቆ የሚፈልገውን ሲቲን በትልቁ ለመቀናቀን ማሰቡን ያሳበቀ ይመስላል። 

በሌላ በኩል በተደጋጋሚ ልቡ ከቀድሞው አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ዳግም ለመቀላቀል ማቆብቆቡ የተነገረለትን ሳንቼዝን በተመለከተ ሲቲዎች በአርሰናል የተጠየቁትን 35 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን በሰሜን ለንደኑ ክለብ በኩልም የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ ተስፋ አድርገዋል።

ነገርግን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የኢምሬትስ ውሉ የሚያበቃውን ቺሊያዊ አጥቂ በተመለከተ የዩናይትድ ጥያቄ ጠንከር ብሎ የሚቀጥል ከሆነ ሲቲዎች የተጠየቁትን ዋጋ ከመክፈል ውጪ አማራጭ እንደማይኖራቸው ይታመናል።

በ 2014 አርሰናልን በ 35 ሚሊዮን ፓውንድ የተቀላቀለው ሳንቼዝ በሶስት አመት ከግማሽ የኢምሬትስ ቆይታው 30 ግቦችን ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ሲያስቆጥር 17 የግብ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል።

Advertisements