መንስኤ / ቫንዲይክ ሊቨርፑልን ያስቀደመበትን ምክንያት ገለፀ

ቨርጂል ቫንዳይክ ከቼልሲና ማንችስተር ሲቲ አስቀድሞ ለሊቨርፑል ለመፈረም ያበቃው የክለቡ ሁኔታና መጠን እንደሆነ ገለፀ።  

ሆላንዳዊው ተጫዋች ባለፍነው ክረምት ወደአንፊልድ ለማምራት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቢቀርብ ለተከላካይ ተጫዋች ክብረ ወሰን የሆነ የዝውውር ገንዘብ በሆነ የ 75 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ከሰሞኑ ሊቨርፑልን መቀላቀል ችሏል።

ሊቨርፑልን ከመቀላቀሉ በፊትም ባሳለፍነው ሳምንት ላይ የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቹን ለማስፈረም ፈልገው የነበረ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ የአንፊልዱ ክለብ ያቀረበውን ዋጋ ለማቅረብ ባለመቻላቸውና የተጫዋቹ ልብ ወደቀያዩቹ በማዘንበሉ ከእንቅስቃሴ ተገተዋል።

ቫንዳይክ በሰጠው መግለጫም “እንደማስበው የክለቡ መጠን፣ ደጋፊዎቹ፣ ተጫዋቾቹ፣ አሰልጣኙ እና አጠቃላይ ሁኔታው አስደናቂ ነው።  

“በአንፊልድ የሚደረግ እያንዳንዱ ጨዋታዎች የተለዩ ናቸው። ለክለቡ ለመጫወት ደስተኛ ነኝ።” ሲል ሊቨርፑልን ከሌሎች ክለቦች ያስቀደመበትን ምክንያት ይፋ አድርጓል።

ቫንዲይክ የወጣበት ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በቀጣይ በሚኖረው የሊቨርፑል ቆይታው ላይ ተፅዕኖ ይፈጥርበት እንደሆነ ተጠይቆም ምንም አይነት ተፅዕኖ እንደማይኖረው አስረድቷል።

“የዝውውር ሂሳቡ ድንጉጥ አያደርገኝም። ሊቨርፑል ያንን ያህል ገንዘብ ለእኔ መክፈሉ እስካሁን እንደነበረው ጠንክሬ እንድሰራ ተጨማሪ ማበረታቻ ነው የሚሆነኝ። ያንን መቀየር አልችልም” በማለት ሆላንዳዊው ኮከብ መልሷል። 

Advertisements