ስኬት / ሀሪ ኬን ለስድስተኛ ጊዜ የወሩ ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር ተቀዳጀ

skysports-harry-kane-tottenham_3906939

የቶትነሀሙ አጥቂ ሀሪ ኬን ለስድስተኛ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ የወሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ በመመረጥ የስቴቨን ጄራርድን ክብረ ወሰን ተጋርቷል፡፡

ኬን ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ስቶክ ላይ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ሲችል ቡድኑ ከበርንሌይ እና ሳውዝአምፕተን በነበረው ጨዋታም ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ከዚህ ቀደም በአንድ ይፋዊ የዘመን አቆጣጠር (2017) አለን ሺረር 39 ግቦችን በማስቆጠር የያዘውን ክብረ ወሰን መስበር ሲችል በ 2017 በብሔራዊ ቡድንና በክለብ ቆይታው ያስቆጠራቸው 56 ግቦችም ሊዮነል ሜሲን በመብለጥም በቀዳሚ ኮከብ ግብ አግቢነት አመቱን በስኬት እንዲያጠናቅቅ አስችሎታል፡፡

የ 24 አመቱ ተጫዋች የወሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ከተመረጠ በኋላም የቀድሞውን የሊቨርፑል እና እንግሊዝ አምበል ጄራርድን ክብረ ወሰን በመጋራቱ የተሰማውን ስሜት “በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡ በጣም ኩራት ተሰምቶኛል፡፡ 

“የእኔ ምርጡ ግብ የምለው የውድድር ዘመኑን የግብ ክብረ ወሰን የሰበርኩበትና ሳውዝአምፕተን ላይ ያስቆጠርኩት ነው፡፡” በማለት አጋርቷል፡፡

በተያያዘ መረጃም ጀርሜንዴ ዴፎ በርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ባደረገውና 2-2 አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ ያስቆጠረው ግብ የወሩ ምርጥ ግብ ተብሎ ተሰይሟል።

Advertisements