ኤዲን ሃዛርድ ስለቼልሲ ቤት ቆይታው ተናገረ


የሰማያዊዎቹ 10 ቁጥር ለባሽ ቤልጅየማዊው ኤደን ሃዛርድ ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሰፊው መያያዙን ተከትሎ በፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን ቼልሲ ያለውን ቆይታ በተመለከተ አቋሙን አሳውቋል፡፡

ትናንት ምሽት በለንድን የተደረገውን የቦስተን ሴልቲክንና ፊላደልፊያ ጨዋታ ለመታደም ከማንችስተር ሲቲዎቹ ኬቨን ዴብሩይን እና ቤንጃሚን ሜንዲ ጋር ለመመልከት የታደመው ሃዛርድ እግረ መንገዱን ከሚረር ጋር ባደረገው ቆይታ በሰማያዊዎቹ ቤት ውሉን ለማራዘም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ሃዛርድ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ በቸለሰበት በዚህ ንግግሩ ከሱ በተጨማሪ የአገሩ ልጅ የሆነው ቲቦ ኮርቶዋም በምህራብ ለንደን ያለውን ኮንትራት በእርግጠኝነት እንደሚያራዝም ተናግሯል፡፡

ለሰማያዊዎቹ ደጋፊዎች አስደሳች የሆነውን ዜና የቸናገረው “አዎ! መጀመሪያ ኮርቶዋ ይፈርማል ፤ ከሱ ቀጥሎ ደሞ እኔ የምፈርም ይሆናል ” በማለት ነበር፡፡

በቼልሲ ቤት የሁለት አመት ቀሪ ውል ያለው ኮከብ በውድድር አመቱ ጅማሮ ላይ ድንቅ የጎል ማስቆጠር ግስጋሴ የነበረው ቢሆንም ባለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ግን አንድ ጎል ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው፡፡

ቼልሲ የሳምንቱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን ነገ ቅዳሜ ከሌስተር ሲቲ ጋር የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Advertisements