ፔፕ ጋርዲዮላ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተሰኙ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የታህሳስ ወር ምርጥ አሰልጣኝ በመሰኘት ሽልማቱን ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ የመጀመሪያው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

በካታሎኒያዊው አሰልጣኝ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ በታህሳስ ወር ካደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች በሊጉ ላይ የሚያደረገውን አስገራሚ ጉዞ እስቀጥሎ ስድስቱን በማሸነፍ እና በአንዱ ብቻ በአቻ ውጤት ተለያይቷል።

ሲቲ በውድድር ዘመኑ በሙሉ አራት ነጥቦችን ብቻ የጣለ ሲሆን፣ በዚህ ወጥ የሆነ ድንቅ ውጤቱም አሰልጣኙ ጋርዲዮላ ወርሃዊ ሽልማቱን በመስከረም፣ ጥቅምት እና ህዳር ወራትም አሸናፊ መሆን ችለዋል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በድረገፁ ከተመልካቹ በሚሰበስበው ድምፅ በየወሩ ምርጥ አሰልጣኝ፣ ምርጥ ተጫዋችና ምርጥ ግብ እንደሚያስመርጥና እንደሚሸልም ይታወቃል።

Advertisements