ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ሲቲ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

የቀዮቹ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ፣ ተጫዋቻቸው ኮቲንሆ አንፊልድን ከለቀቀ ወዲህ ክለቡ ብራዚላዊውን ተጫዋች ዘንግቶ በኢትሃድ የደረሰበትን የ5ለ0 ሽንፈት እንዲበቀልና ያለተጫዋቹ አዲስ ህይወት እንዲጀምር በመግለፅ ይህን ጨዋታ ትኩረት ሰጥተው የሚያደረጉት እንደሆነ ገልፀዋል።

የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በውድድር ዘመኑ ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች 20 ጨዋታ በማሸነፍ እና ሁለቱን ብቻ በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ያለሽንፈት እዚህ ድረስ የዘለቀ ሲሆን፣ ነገር ግን እ.ኤ.አ. ከ2003 ግንቦት ወር አንስቶ በሊጉ ማሸነፍ ባልቻለበት አንፊልድ ስታዲየም ቀላል ጨዋታ ይጠብቀዋል ተብሎ አይታሰብም። 

ቀን፡ እሁድ ጥር 6፣ 2010 ዓ.ም
ሰዓት፡ ምሽት 1፡00 
ሜዳ፡ አንፊልድ (ሊቨርፑል)

ባለፈው የውድድር ዘመን በዚሁ ሜዳ
፡ ሊቨርፑል 1 ማን ሲቲ 0

የጨዋታው ዳኛ
፡ አንድሬ ማሪነር (ዳኛው በዚህ የውድድር ዘመን አጫወቱ 15፣ ቢጫ36 ቀይ2፣ በአማካኝ በየጨዋታው 2.67 ካርዶች)

ግምታዊ አሰላለፎች

ሊቨርፑል

ተቀያሪዎች፡ ካሪዩስ፣ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ላላና፣ ሎቭረን፣ ክላቫን፣ ሚልነር፣ ፍላናጋን፣ ግሩጂች፣ ዉድበርን፣ ሶላንኬ፣ ማርኮቪች፣ ኢንግስ
ማሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡  የሉም
ጉዳት ያለባቸው፡ ሞሬኖ (የቁርጭምጭሚት)፣ ሄንደርሰን (የቋንጃ)፣ ስተሪጅ (የቋንጃ)፣ ዋርድ (የጀርባ)፣ ክላይን (የጀርባ)
ቅጣት ያለባቸው፡  የሉም
ወቅታዊ ውጤቶች፡ አቻ፣ ድል፣ አቻ፣ ድል፣ ድል፣ ድል፣ ድል
ካርዶች፡ ቢጫ26፣ ቀይ1
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች፡ መሐመድ ሳላህ 17

ማንችስተር ሲቲ

ተቀያሪዎች፡  ብራቮ፣ ቱሬ፣ አዳራቢዮ፣ ዲያዝ፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ዳኒሎ፣ ጉንዶጋን፣ ማንጋላ፣ ኮምፓኒ፣ ዚኒቼንኮ 
መሰፋቸው የሚያጠራጥሩ፡ ኮምፓኒ (በባት ጉዳት) 
ጉዳት ያለባቸው፡ ኼሱስ (የጉልበት)፣ ፎደን (የቁርጭምጭሚት)፣ ሜንዲ (የጉልበት) 
ቅጣት ያለባቸው፡ የሉም
ወቅታዊ ውጤቶች፡ ድል፣ ድል፣ ድል፣ ድል አቻ፣ ድል
ካርዶች፡ ቢጫ38 ቀይ2
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች፡ ራሂም ስተርሊንግ 14

የሁለቱ ክለቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት

  • ለመጨረሻ ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች: ሊቨርፑል ድል2፣ ማን ሲቲ ድል2፣ አቻ 
  • በፕሪሚየር ሊጉ ግንኙነታቸው: ሊቨርፑል ድል18፣ ማ ሲቲ ድል8፣ አቻ15
  • በሁሉም ውድድሮች ግንኙነታቸው: ሊቨርፑል ድል101፣ ማን ሲቲ ድል54፣ አቻ52
Advertisements