ሪያን ጊግስ የዌልስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተደርጎ ተሾመ

ሪያን ጊግስ የዌልስ ብሔራዊ ቡድን ተደረጎ መሾሙን የሃገሪቱ እግርኳስ ማህበር ዛሬ (ሰኞ) ዕለት በይፋ ገልፅዋል።

የ43 ዓመቱ ጊግስ ሰንደርላንድን ለመቀላቀል ሲሉ በህዳር ወር ብሄራዊ ቡድኑን የለቀቁትን ክሪስ ኮልማንን ተክቶ በአሰልጣኝነት መሾሙን እግርኳስ ማህበሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፅዋል።

ጊግስ እ.ኤ.አ. በ1991 እና 2007 መካከል ባሉት ጊዜያት ለብሄራዊ ቡድኑ 64 ጨዋታዎችን ማሸነፍ የቻለ ቢሆንም ነገር ግን በተለይም የወዳጅናት ጨዋታዎችን ጨምሮ በርካታ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ ባለመሰለፉ በአንዳንድ የዌልስ ደጋፊዎች ትችት ይሰነዘርበታል።

የቀድሞው ተጫዋች የ23 ዓመታት ወርቃማ የእግርኳስ ህይወቱን በ2014 ቋጭቶ፣ በ2013-14 በተሰናባቹ ዴቪድ ሞየስ ምትክ እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ማንችስተር ዩናይትድን በአራት ጨዋታዎች ላይ በጊዜያዉ አሰልጣኝነት መምራት ችሏል።

ጊግስ፣ ሞሪንሆ በ2016 ክለቡን በአሰልጣኝነት ከመረከባቸው በፊት ባሉት ሁለት የውድድር ዘመናት በኦልድ ትራፎርድ የልዊ ቫን ኻል ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል።

ኮል ማን ዌልስን በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ እስከግማሽ ፍፃሜ ድረስ በአሰልጣኝነት መምራት ችለው የነበረ ቢሆንም በዚህ ዓመት ለሚደረገው የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ግን ብሄራዊ ቡድኑ ማሳለፍ ሳይቻላቸው ቀርተዋል።

Advertisements