ስቶክ ሲቲ ፖል ላምበርትን በአሰልጣኝነት ቀጠረ

ስቶክ ሲቲ  ፖል ላምበርትን አዲስ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን በይፋዊ ድረገፁ ገልፅዋል።

የቀድሞው የዎልቨርሃምፕተን፣ ብላክበር፣ አስቶንቪላና ዎልቭስ አሰልጣኝ ላምበርት ስቶክ ሲቲ በኤፍኤ ዋንጫው ሶስተኛ ዙር በኮንቨንትሪ ሲቲ ሽንፈት ከደርሰበት በኋላ ከክለቡ የአሰልጣኝነት ስራቸው የተሰናበቱትን ማርክ ሂዩዝን ተክተው ፖተርሶቹን በዋና አሰልጠኝነት የሚረከቡም ይሆናል። 

ላምበርት በክለቡ ለሁለት ዓመታት ከግማሽ በክለቡ የሚያቆያቸውን የኮንትራት ስምምነት መፈረማቸውንም ክለቡ በመግለጫው ገልፅዋል።

ስቶኮች በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ነጥብ ዝቅ ብለው በ18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቢሆንም፣ በ11ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ዌስት ሃም ግን ያላቸው ርቀት አምስት ነጥብ ብቻ ነው። 

ፖተርሶቹ ዛሬ (ሰኞ) ምሽት ወደኦልትራፎርድ ተጉዘው ማንችስተር ዩናትድን የሚገጥሙ ቢሆንም፣ አዲሱ አሰልጣኝ ላምበርት ግን እስከነገ (ማክሰኞ) ድረስ ክለቡን በኃላፊነት አይረከቡም። በመሆኑም ለምሽቱ ጨዋታ ኤዲ ኒድዝዊኪ በኬቨን ረስል እና አንዲ ኩይ እየታገዙ ቡድኑን የሚመሩ ይሆናል።

Advertisements