የዕለተ ሰኞ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

ለአንድ ወራት የሚዘልቀው የአውሮፓ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ገበያ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀንም እንደደራ ቀጥሏል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም የአውሮፓ አባይት ጋዜጦች በዕለቱ ይዘዋቸው የወጡ የዝውውር ወሬዎችን እንደሚከተለው አሰናድታለች።

ሪያል ማድሪድ ኔይማርን በሮናልዶ የመቀየር ፍላጎት አለው

የስፔኑ ጋዜጣ ካዴና ሰር እንደዘገበው ከሆነ ሪያል ማድሪድ የዓለም ዋንጫው እንደተጠናቀቀ ኔይማርን ከፒኤስጂ ለማስፈረም ጥረት የሚያደረግ ይሆናል። የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ብራዚላዊውን ተጫዋች አብዝተው የሚፈልጉት በመሆኑም ክርስቲያኖ ሮናልዶን የዝውውሩ አካል አድርገው ለማቅረብ ፈቀደኛ ናቸው።

ሞራ ፒኤስጂን በጥር ወር እንደሚለቅ ገለፀ

ሉካስ ሞራ በማንችስተር ዩናይትድ እንደሚፈለግ በሚወራበት በዚህ ወቅት ፒኤስጂን በጥር ወር ሊለቅ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ገልፅዋል።

ሌስተሮች ማህሬዝን ለማቆየት ቁርጠኛ ሆነዋል

እንደቀበሮዎቹ አሰልጣኝ ክላውድ ፑየል ንግግር ከሆነ ሌስተር ሲቲዎች ሪያድ ማህሬዝን ከጥር ወር ባሻገርም በክለባቸው ለማቆየት ቁርጠኛ ናቸው።

ጊግስ የዌልስ አሰልጣኝ ሊሆን ነው

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ኮከብ ሪያን ጊግስ ዛሬ (ሰኞ) የዌልስ አሰልጣኝ ተደረጎ ሊሾም መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዞርክ በኦቦምያንግ ባህሪ ሃሳብ ገብቷቸዋል

የዶርትሙንዱ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር፣ ማይክል ዞርክ ክለቡ እሁድ ከዎልፍስበርግ ጋር 0-0 ባጠናቀቀበት ጨዋታ ላይ እንዳይሰለፍ በተደረገው የክለቡ አጥቂ ፒየር-ኤመሪክ አባምያንግ ባህሪ ሃሳብ እንደገባቸው ገልፀዋል። ተጫዋቹ በአርሰናል እንደሚፈልገ ይታወቃል።

አርሰናል ማልኮምን በ44 ሚ.ፓ ለማስፈረም ተቀርበዋል

አርሰናል የቦርዶውን የፊት ተጫዋች ማልኮልምን በ44 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ተቃርቧል።

ካልዴሮን: ሮናልዶን መለዋወጥ ሃሳብን ማስቀየሻ ታክቲክ ነው 

ክርስቲያኖ ሮናልዶን በኔይማር የመቀየር የዝውውር ስምምነት የሪያል ማድሪድን ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ለማስቀየስ የሚደረግ “ቂላቂል” ሙከራ እንደሆነ የቀድሞው የክለቡ ፕሬዝዳንት ረሞን ካልዴሮን ተናግረዋል።

ኢካርዲ ወደማድሪድ ሊዛወር ነው

የኢንተሩ ኢካርዲ ወደሪያል ማድሪድ ለመዛወር ተዘጋጅቷል።

the guardian

 • • ቼልሲ  አንዲ ካሮልን በዚህ ወር ከዌስትሃም የማስፈረም ፍላጎት አለው።
 • • ክሪስታል ፓላሶች የፊዮረንቲናውን አጥቂ ክሁማ ባባካርን በ15 ሚ.ፓውንድ ዋጋ ስምምነት እንደሚያስፈርሙት ተስፋ አድርገዋል።

daily mail

 • • የኤቫርተኑ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ቲዮ ዋልኮትን በዚህ ወር ከአርሰናል ማስፈረሙ የሚሳካላቸው ቢሆን እንኳ የመሃል አጥቂነት ሚና  እንደሚሰጡት ማረጋገጫ አይሰጡትም።
 • • የሊቨርፑሉ መሃመድ ሳላህ ከዚህ ቀደም በ2.5 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለበርካታ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለሽያጭ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ፍላጎታቸውን የገለፁት ግን ኸል ሲቲ እና ስቶክ ሲቲ ብቻ ነበሩ።

daily star

 • • ማንችስተር ዩናይትዶች ከዘጠኝ ወራት ድብቅ ፍላጎት በኋላ አሌክሲ ሳንቼዝን ለማስፈረም ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛሉ። 

daily telegraph

 • • አርሰናል ሄነሪክ ሚክሂታሪያንን የሳንቼዝ የዝውውር አካል አድርጎ ለማስፈረም በመፈለጉና የዶርትሙንዱን ፒየር ኤምሪክ ኦባምያንግ ለማዛወር ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ አሌክሲ ሳንቼዝ ማንችስተር ዩናይትድ ለመቀላቀል ተቃርቧል።
 • • ማርቲን ኦኔል ከአየርላንድ እግርኳስ ማህበር ጋር ያለቸውን የቃል ስምምነት ላለማፍረስ ሲሉ ከስቶክ ሲቲ የቀረበላቸውን የአስልጠኝነት ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል።
 • የኦሌን ውሳኔን ተከትሎም ስቶኮች ትኩረታቸውን ወደአስቶንቪላው አሰልጣኝ ፖል ላምበርት አዙረዋል።

the sun

 • • ፒኤስጂ የቼልሲውን ኮከብ ንጎሎ ካንቴን የክረምቱ አብይ የዝውውሩ ዒላማ ማድረጉ ተዘግቧል።
 • • ስዋንሲዎች የክለባቸው ክብረወሰን በሆነ የዝውውር ዋጋ በቱርኩ ክለብ ፊነርባቼ ጭምር የሚፈለገውን የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ኬቨን ጋሜሮን ለማስፈረም አቅደዋል።
 • • ሻልከዎች የቼልሲውን የግራ ተከላካይ ባባ ራህማንን ለሁለተኛ ጊዜ በውሰት ለመውሰድ ንግግር እያደረጉ ነው።
 • • ኒውካሰሎች የክሪስታል ፓላሱን የግራ ተከላካይ፣ ፓፔ ሶሬን ቀሪውን የውድድር ዘመን በውሰት ለማስፈረም ተቃርበዋል።

daily mirror

 • • ማንችስተር ዩናይትዶች ዴቪድ ደ ኽያ ቀሪ የእግርኳስ ህይወቱን በክለቡ እንዲያጠናቅቅ ለማድረግ ሲሉ በሳምንት 250,000 ፓውንድ ደመወዝ ሊያቀርቡለት ነው።
 • • ጆዜ ሞሪንሆ በቲሞቲ ፎሱ-ሜንሳህ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሊያሳልፉ ነው።
 • • ባየርሙኒኮች የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹን ሊኦን ጎርዝከን ከሊቨርፑል እና አርሰናል ማንጋጋ ሊመናትፉ አቅደዋል።
 • • ቶተንሃሞች የስቴቬናጁን ወጣት ተጫዋች ቤን ዊልሞትን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ላይ በራስ መተማመን ተሰምቷቸዋል።
 • • ዋትፎርድ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ስቶክ የጋላታሳራዩን አማካኝ ባዱ ንዳዬን ለማስፈረም ፈልገዋል።

daily express

 • • አንቶኒዮ ኮንቴ ቼልሲን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚለቁ ከሆነ ለሁለተኛ ጊዜ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ለመሆን ወደጣሊያን መመለሳቸውን አላስተባበሉም።

daily record

 • • ቦርንማውዞች የቼልሲውን ወጣት አጥቂ ቻርሊ ሙሶንዳን በውሰት ለማስፈረም በፉክክሩ ሴልቲክን ለመርታት ተዘጋጅተዋል።
 • • ሴልቲኮችም ሙሶንዳን ለማዛወር የሚያደርጉት ሙከራ ካልተሳካ የሻልከውን አጥቂ ፍረንኮ ዲ ሳንቶን ለማስፈረም ጥረት ሊያደረጉ ይችላሉ።

  Advertisements