ጉዳት / ኡስማን ዴምቤሌ በጉዳት እስከ አንድ ወር ከሜዳ ይርቃል

96.8 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት ወደ ባርሴሎና ያቀናው ወጣቱ ኡስማን ዴምቤሌ በድጋሚ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ይርቃል።

<!–more–>

ባርሴሎና ከ 10 አመት በኋላ በአንዬታ ስታድየም ሪያል ሶሲዳድን በማሸነፍ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ባሳካበት የትናንት ምሽት ጨዋታ ዴምቤሌ ጉዳት አጋጥሞታል።

የአለም ሶስተኛው ውዱ ተጫዋች የሆነው ዴምቤሌ ባለፈው መስከረም ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ ከተመለሰ በኋላ ያደረገው አራት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር።

ነገርግን በእሁድ ምሽቱ ጨዋታ በድጋሚ በግራ እግሩ ላይ ያጋጠመው የቋንጃ ጉዳት እስከ አንድ ወር ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል።

ክለቡ በመግለጫውም ከህክምና ምርመራ በኋላ ተጫዋቹ የቋንጃ ጉዳት እንዳጋጠመው እና ከሶስት እስከ አራት ሳምንት ከጨዋታ ውጪ እንደሚሆን አሳውቋል።

Advertisements