የዕለተ ማክሰኞ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

ለአንድ ወር የሚዘልቀው የአውሮፓ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ከተከፈተ ጊዜ አንስቶ በአስራአምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ድንገተኛ እና የሚጠበቁ ዝውውሮች ተከናውነውበታል። በተቀሩት የወሩ አጋማሽ ቀናትም ተመሳሳይ ዝውውሮች ይከናወኑበታል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም በዛሬው ዕለት በአውሮፓ አበይት የስፖርት ጋዜጦች የተዘገቡ አጫጭር እና በርከት ያሉ የዝውውር ወሬዎችን እንዲህ አሰናድታለች።

የጣሊያን የዝውውር ወሬዎች

• የሳውዛምፕተኑ አጥቂ ማኖሎ ጋቢያዲኒ የቦሎኛ የዝውውር ዒላማ ውስጥ መግባቱን ስካይ ኢታሊያ ዘግቧል። የተጫዋቹ ወኪል የሆነው ሪካርዶ ኦርሶሊኒ ደንበኛውን ወደጣሊያን የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ቢሆንም ሳይንቶቹ ግን በዚህ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ላይለቁት ይችላሉ።

• ሪያል ማድሪድ 110 ሚ.ዩሮ (97.7 ሚ.ፓ) የሆነውን የማሪዮ ኢካርዲ የውል ማፍረሻ ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነው። ሎስ ብላንኮዎቹ የፊት ክፍላቸውን ለማጠናከር የኢንተሩን አጥቂ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው የዘገበው ኮሪየር ዴሎ ስፖርት ጋዜጣ ነው።

• እንደጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ራጃ ኒያንጎላን ከጉዋንዡ ኤቨርግረንዴ ጋር በግል ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ የደረሰ ቢሆንም ዝውውሩን የቻይናው የኮምኒት ፓርቲ ሊያግደው ይችላል። የቻይና መንግስት የሃገሪቱን የገበያ ግሽበት ለመቀነስ ሲል እጅግ የተጋነኑ የዝውውር ወጪዎችን የመግታት ፍላጎት አለው። በመሆኑም የሮማው አማካኝ ዝውውር በጥር ወር ባይሳካ እንኳ በመጪው ክረምት ግን ሊፈፀም ይችላል።

የጀርመን የዝውውር ወሬዎች

ፒየር-ኤመሪክ ኦባመያንግ ዝውውር ማድረግ የሚችልበትን ፈቃድ እንዲሰጠው ለዶርትሙንድ ጥያቄ ማቅረቡን ቢልድ ጋዜጣ ዘግቧል። የፊት ተጫዋቹ የአርሰናል የዝውውር ዒላማ ነው ተብሎ እንደሚታመንም የጋዜጣው ዘገባ ጨምሮ አመልክቷል።

• ጁቬንቱሶች በክለባቸው በውሰት ላይ የሚገኘውን የሻልከውን ተከላካይ ቤነዲክት ሆወደስን በቋሚነት ማስፈረም እንደሚፈልጉ የዘገበው አሁንም ቢልድ ነው።

የስፔን የዝውውር ወሬዎች

• ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከክለቡ ፕሬዝዳንት ፎሎረንቲኖ ፔሬዝ ጋር መቃቃር ውስጥ ከገባ ወዲህ ሪያል ማድሪድን የመልቀቅ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘገባ አመልክቷል። ፓርቱጋላዊው የፊት ተጫዋች ከክለቡ ጋር ያለው ኮንትራት ከሊዮኔል መሲና ኔይማር ያነሰ መሆኑ አላስደሰተውም። በአሁኑ ጊዜ የቀረበለት ተጨባጭ የዝውውር ጥያቄ እሱን ከማይማርከው ከወደቻይና እንደሆነም የሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘገባ አመልክቷል።

• ሮናልዶ ሪያል ማድሪድን በቀጣዩ ክረምት የመልቀቅ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑ ማንችስተር ዩናይትድ ፓርቱጋላዊውን ኮከብ ዳግም ወደኦልትራፎርድ የሚያመጣበትን ሁኔታ እንዲያጤንበት እንዳደረገው የአስ ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል። ቀያይ ሰይጠኖቹ ተጫዋቹን ወደማንችስተር ዩናይትድ እንዲመለስ የሚያስችል የፋይናስ አቅም ቢኖራቸውም ለ33 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር 88 ሚ.ፓውንድ እና ለዓመታዊ ደመወዙ 44 ሚ.ፓውድን ወጪ ማድረጉ ግን ትልቅ አደጋ እንደሚኖረው ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

• ኔይማር የሪያል ማድሪድ የዝውውር ዒላማ ውስጥ ቢገባም ተጫዋቹን በትልቅ የዝውውር ዋጋ ከፒኤስጂ ማስፈረሙ ግን ለሎስ ብላንኮዎቹ አስቸጋሪ እንደሚሆን ያውቁታል። በዚያ ላይ የተጫዋቹ ክለቡን መቀላቀል በተጫዋቾቻቸው የደመወዝ መዋቅር ላይ ቀውስ የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ በሌሎች የክለቡ ተጫዋቾች ላይ ቅሬታን እንደሚፈጥር የዘገበው ስፖርት ጋዜጣ ነው።

• ሪያል ማድሪዶች ምንም እንኳ ወቅታዊ አቋማቸው መጥፎ ቢሆንም የእቅድ ለውጥ በማድረግ በጥር ወር ምንም ዓይነት ተጫዋች ላያስፈርሙ እንደሚችሉ ማርካ ዘግቧል።

የፈረንሳይ የዝውውር ወሬዎች

የስዋንሲ ሲቲ የዝውውር ዒላማ ውስጥ የገባው ኬቨን ጋሜሮ አትሌቲኮ ማድሪድን ስለመልቀቅ እያሰበ እንደማይገኝ የለኪፕ ጋዜጣ ዘገባ ያመለከተ ሲሆን ፈረንሳዊው ተጫዋች ቢያንስ እስከመጪው ክረምት ድረስ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ለመቆየት ውሳኔ ላይ መድረሱንም ዘገባው አክሎ ገልፅዋል።

• ኢሚሊያኖ ሳላ ለናንተስ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ሲል ወደብራይተን ለመዛወር የቀረበትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ለኪፕ ዘግቧል።

የእንግሊዝ ጋዞጦች የዝውውር ወሬዎች

daily telegraph

 • አርሰናል ፒየር-ኤመሪክ ኦባመያንግን ለማስፈረም ተቃርቧል። 

the guardian

 • ኤምሬ ቻን ምንም እንኳ በጁቬንትስ የሚፈለግ ተጫዋች ቢሆንም ለሊቨርፑል አዲስ ስምምንት ሊፈርም ይችላል።
 • ኤቨርተኖች ቲዮ ዋልኮትን በ20 ሚ.ፓ የዝውውር እንደሚያስፈርሙት ተስፋ አድርገዋል።

daily mirror

 • አዲሱ የስቶክ አሰልጣኝ ፓል ላምበርት ፓተርሶቹን ከወራጅ ቀጠና ማትረፍ የሚችሉበት የዝውውር ገንዘብ የሚቀርብላቸው ይሆናል። 
 • ዌስት ሃሞች አንዲ ካሮል ወደቼልሲ በውሰት እንዲያመራ የሚያደረገውን ጥያቄ ቸል አይልም በሚል ስጋት ገብቷቸዋል።

daily express

 • አማንዳ ስታቬስሌይ ኒውካሰልን ከባለቤቱ ማይክ አሽሊ ለመግዛት ጥያቄዋን ወደ300 ሚ.ፓ ከፍ አድርጋለች።
 • ሊቨርፑሎች ጄምስ ማዲሰንን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከኖርዊች ለማዛወር ውጥን ይዘዋል።

daily mail

 • አዲሱ የዌልስ አአልጣኝ ሪያን ጊግስ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አጋሩ ፓል ስኮልስን የዌልስ የስልጠና ክፍልን እንዲቀላቀል ለማድረግ እንቅስቃሴ ሊጀምር ነው።
 • ሆዜ ሞሪንሆ ምንም እንኳ አሌክሲ ሳንቼዝን ለማዛወር ሌሎች ክለቦችም ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልፁም ዩናይትድ የአርሰናሉን ኮከብ ለማስፈረም ግን “በራስ መተማመናቸው” ዝቅ ያለ እንዳልሆነ ተናግረዋል። 
 • ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስፔኑ ኃያል ክለብ ክህደት እንደተፈፀመበት በመግለፅ በሪያል ማድሪድ የሚኖረውን የወደፊት ቆይታ ጥርጣሬ ውስጥ ከቶታል።
 • ቶተንሃሞች ቶቢ አልደርዊረልድ አዲስ ኮንትራት ስለሚፈርምበት ጉዳይ ከተጫዋቹ ጋር ተቀምጠው መነጋገር ጀምረዋል።

daily star

 • አዲሱ የስቶክ አሰልጣኝ ፓል ላምበርት ፓተርሶቹን ከወራጅነት አደጋ የሚያተርፉ ከሆነ 1.5 ሚ.ፓ ተጨማሪ ጉርሻ የሚያገኙ ይሆናል። 
 • ፔፕ ጋርዲዮላ ኢኒጎ ማርቲኔዝን በ27 ሚ.ፓ ከሪያል ሶሴዳድ ለማስፈረም ጥያቄያቸውን ወደፊት ገፍተውበታል።
 • ቦርንማውዞች የአርሰናሉን ቲዮ ዋልኮትን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር ከኤቨርተን እና ሳውዛምፕተን ጋር ተቀላቅለዋል።
 • በርንሌዮች የብራይተኑን የክንፍ ተጫዋች ሶሊ ማርችን የዝውውር ዒላማቸው ውስጥ አስገብተውታል። 
 • የስዋንሲ የዝውውር ዒላማ ውስጥ የሚገኘው ርያን ፍሬድሪክስ ከፋልሃም የቀረበለትን አዲስ የዝውውር ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ተናግሯል።
 • የኸደርስፊልዱ አማካኝ ጃክ ፓይኔ የሊግ ዋኑን ክለብ፣ ብላክበርንን በውሰት ሊቀላቀል ነው።
 • የክሪስታል ፓላሱ የፊት ተጫዋች ኬሺ አንደርሰን በስዊንደን ያለውን የውሰት ቆይታ ወደቋሚነት የሚለውጥበትን ዕድል ውድቅ አድርጓል።
 • ሳውዛምተኖች ስዊዘርላንዳዊውን የዩዴኔዜ የቀኝ መስመር ተከላካይ፣ ሲልቫንድ ዊድመርን ለማስፈረም ፈልገዋል።
 • ዋትፎርዶች በሰንደርላንድ ያልተሳካለትን ዲዲየ ንዶንግን በውሰት ለመውሰድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የመስተጓጎል አደጋ ተጋርጦበታል።

the sun

 • ማንችስተር ዩናይትዶች አሌክሲ ሳንቼዝን ለማስፈረም አንቶኒ ማርሻልን የዝውውሩ አካል የማድረጉን ጉዳይ ውድቅ ማድረጋቸው ተዘግቧል።
 • ዌስት ብሮሞች ለፉልሃሙ አምበል ቶሚ ኬርኒ ዝውውር 12 ሚ.ፓ ሊያቀርቡ ነው።
 • አውስትራሊያዊው ቲም ካሂል ወደቀድሞ ክለቡ ሚልዎል ዳግመኛ ሊመለስ ይችላል።
Advertisements