የዕለተ ረቡዕ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

የአውሮፓ የጥር ወር የዝውውር ገበያ የእንግሊዝ ጋዜጦች የዕለተ ረቡዕ አጫጭር የዝውውር ወሬዎችን እነሆ ብለናል።

the sun

 • እንደቦርዶው አሰልጣኝ፣ ጆሲሊን ጎርቬኔች ንግግር ከሆነ የአርሰናል የዝውውር ዒላማ የሆነው ማልኮም ሊቨርፑልን ሊቀላቀል ይችላል።

daily mirror

 • የ28 ዓመቱ ጋቦናዊው አጥቂ ፒየር-ኤመሪክ አውባሜያንግ ወደአርሰናል የሚያደረገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዶርትሙንዶችን እየተማፀነ ይገኛል።
 • ቼልሲ የሮማውን ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪን ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ነው።
 • በመጪው ክረምት ክለቡን በነፃ ሊለቅ የሚችለው የ26 ዓመቱ እንግሊዛዊው የአርሰናል አማካኝ ጃክ ዊልሼር ከክለቡ አዲስ ኮንትራት እንዲቀርብለት የሚደረግለትን ሙሉ የህክምና ምርመራ በሚገባ ማለፍ እና ከክፍያው 20 በመቶ ቅናሽ ማድረግ ይኖርበታል። 

  daily mail

  • ሄነሪክ ሚክሂታሪያን በማንችስተር ዩናይትድ ቀጣይ ህይወት እንደማይኖረው መቀበሉን ተከትሎ የአሌክሲ ሳንቼዝ የዝውውር የልውውጥ አካል በመሆን ወደአርሰናል ለመዛወር ተቃርቧል።
  • የ28 ዓመቱ እንግሊዛዊው ተጫዋች ቲዮ ዋልኮት በፊንች ፋርም የተደረገለትን የህክምና ምርመራ በስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ ከአርሰናል ወደኤቨርተን የሚያደረገውን ዝውውር ሊያጠናቅቅ ተቃርቧል።
  • ሲሞን ሚኞሌ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተደረገው የእሁድ ምሽቱ ጨዋታ ላይ በተቀያሪነት እንዲቀመጥ ከተደረገ በኋላ ስለሊቨርፑል የወደፊት ዕጣ ፈንታው የግድ ማጤን እንደሚኖበት ሳይደብቅ ተናግሯል።
  • ፉልሃሞች ከኮንትራት ነፃ የሆነውን የ31 ዓመቱን አርጄንቲናዊ የክንፍ ተጫዋች፣ ሰባስቲያን ሌቶን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር እየተነጋገሩ ነው።

  daily telegraph

  • አንቶኒዮ ኮንቴ ሮዝ ባርክሌይን በኖርዊቹ ጨዋታ ላይ ለክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታውን እንዲያደርግ የሚችልበት ዕድል ከመስጠተቸው በፊት የወዳጅነት ጨዋታ ሊያዘጋጁለት ስለሚችሉበት ጉዳይ መልሰው እንዲያስቡ ተገደዋል።
  • ቼልሲዎች የ29 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ አንዲ ካሮልን በቋሚናት ለማፈረም ለዌስት ሃሞች ጥያቄ አቅርበዋል።

  the independent

  • ቼልሲ የአርሰናሉን አሌክሲ ሳንቼዝን እንደማይፈልግ አንቶኒዮ ኮንቴ ገልፀዋል።
  • ሊቨርፑሎች ወደቶተንሃም ለማምራት ከስምምነት ላይ መድረሱን የተዘገበለትን የስቴቨኔጁን ተከላካይ ቤን ዊልሞትን ለማስፈረም የሚያደረጉትን ጥረት ቀጥለውበታል። 

  daily star

  • ሪያል ማድሪዶች ክርስቲያኖ ሮናልዶን ለመልቀቅ ፈቃደኞች ሲሆኑ፣ ተጫዋቹን ለማስፈረምም ማንችስተር ዩናይትድና ፒኤስጂ የሚያድረገትን ፍልሚያ ለመመልከት ፍላጎት አላቸው።
  • ዌስት ሃሞች ለካሮል የሚቀርብላቸውን 20 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ ለመስማት ፈቃደኞች ናቸው።
  • የ21 ዓመቱ ሰርቢያዊው የሊቨርፑል አማካኝ ላዛር ማርኮቪች የሚድልስብሮ እና የካርዲፍ የውሰት ዝውውር ዒላማ ውስጥ ገብቷል።
  • የ26 ዓመቱ የሳውዛምፕተን አጥቂ ማኖሎ ጋቢያዲኒ ከቀድሞ ክለቦቹ አንዱ ወደሆነው ቦሎኛ ሊመለስ ይችላል።
  • ቶተንሃም የ21 ዓመቱን እንግሊዛዊ የኖርዊች አማካኝ ጄምስ ማዲሰንን ከሚፈልጉ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። 
  • የ27 ዓመቱ የኒውካሰል የፊት ተጫዋች ድዋይት ጋይል ወደሻምፒዮንሺፑ ክለብ ፉልሃም በ15 ሚ.ፓ ሊዛወር ነው በሚል ስሙ ከክለቡ ጋር ተያይዟል።
  Advertisements