“ሌዮኔል ሜሲ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ የተሻለ ተጫዋች ነው” – ፔሌ

​በብዙዎች የእግር ኳስ ንጉስ እየተባለ የሚሞካሸው ብራዚላዊው ታሪከኛ ፔሌ በሁለቱ የትውልዱ ከዋክብት ላይ ያለውን ሃሳብ ያሳወቀ ሲሆን ከፖርቱጋላዊው ይልቅ አረጀንቲናዊውን እንደሚያስበልጥ ተናግሯል፡፡
ላለፉት አመታት እግርኳሱን በማን አለብኝነት ከተቆጣጠሩት ከሁለቱ ፈርጦች የተሻለው ማነው? የሚለው ጥያቄ ብዙአን የተለያየ ሃሳባቸውን ሲሰጡበት የከረሙ ሲሆን ተረኛው ደግሞ ፔሌ ሆኗል፡፡

ፔሌ ከ ስፖር ቲቪ ጋር ባደረገው ቆይታ ሃሳቡን ሲሰጥ “ከሁለቱ መምረጥ በጣም አስቸጋሪ ሆኖብኛልና ባልመርጥ የተሻለ ነበር ፤ ሆኖም የግድ መምረጥ አለብህ ካላችሁኝ ወደሜሲ አደላለሁ፡፡”

“ጎሎችን ማስቆጠር መልካም ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ጎል ለማስቆጠር የቡድንህ ከባላት እገዛ ያስፈልግሃል ፡፡ ሮናልዶ ጎሎችን በማስቆጠር የተካነ ነው፡፡ ሜሲ ለጎል ኳሶችን በማቀበል ፣ ጨዋታዎችን በመምራትና በመቆጣጠር የተሻለ ነው፡፡በተጨማሪም ጎሎችን ያስቆጥራል፡፡ለቡድኔ የምመርጠው አይነት ተጫዋች ነው”

“ለኔ ሮናልዶ ጥሩ ጎል አስቆጣሪ ሲሆን ሜሲ ደሞ የተሟላ ተጫዋች ነው” በማለት ፔሌ ለባርሴሎናው ኮከብ የሚያደላ ሃሳቡን አጠቃሏል፡፡

Advertisements