አርሰን ቬንገር / የፈረንሳዊው አለቃ መግለጫ በሳንቼዝና ማኪቴሪያን፣ በዊልሻየር፣ በኦቦምያንግ እና ሌሎች የቡድናቸው ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ

የቡድን ዜናዎች

“ባለፈው በነበረው የቦርንማውዝ ጨዋታ በኋላ አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች አሉብን፡፡ የማቲላንድ ኒልስ ነገር ከጉንፋን ጋር በተያያዘ ቅዳሜ መሰለፋቸው አጠራጣሪ ነው፡፡  

“ኮሎንስሊያክ እና ሞንሪያል በቅዳሜው ጨዋታ ሊኖሩን ይገባል፡፡ ኦዚልም ሊመለስልን ይችላል፡፡ 

“ኦሊቬ ዢሩ በበኩሉ ወደሜዳ ለመመለስ አንድ ሳምንት ይቀረዋል፡፡”

በቲዮ ዋልኮት ዙሪያ 

“ቲዮ ያለውን ንቃት፣ ቁርጥኝነት እና በስራው ላይ ያለውን ትኩረት እወድለታለሁ፡፡

“አስታውሳለሁ! እሱ ወደዚህ የመጣው ቀጥታ ከአለም ዋንጫ ውድድር በቀጥታ በ 16 አመቱ ነበር፡፡ በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ ለአርሰናል ግብ አስቆጥሯል፡፡ 

“በተፈጠረው ነገር (በመሸጡ) ተፀፅቻለሁ፡፡ ነገርግን በቅርቡ ጊዜያት በቂ ጨዋታ ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡ በቀጣይ ወደዚህ ሲመጣ ግን ሁሌም ጥሩ አቀባባል እናደርግለታለን፡፡” 

በሳንቼዝና ማኪቴሪያን ዝውውር ዙሪያ 

“ዝውውሩ ሊሳካ ይችላል፡፡ ላይሳካም ደግሞ ይችላል፡፡  ጉዳዩ በዛ ደረጃ ነው ያለው፡፡”

ሳንቼዝ ለአርሰናል በድጋሚ ይጫወታል?

“አዎ! አጋጣሚው የሚገኝ ከሆነ በመጪው ቅዳሜ ሊጫወት ይችላል፡፡”

ዝውውሩ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ሊጠናቀቅ ይችል ይሆን ?

“አዎ! ሊጠናቀቅ ይችላል፡፡ ነገርግን በየትኛውም ሰዓት ነገሮች ላይሳኩ ይችላሉ፡፡ የዝውውር ገበያ እንደዚህ አይነት መልክ ያለው ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ላይ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም፡፡ 

ማኪቴሪያን በሳንቼዝ ቅያሪ ወደቡድኑ የመምጣቱ ነገርስ?

“አዎ! እንደዛ አስባለሁ፡፡ ተጫዋቹን እውደዋለሁ”

የደሞዝ ሁኔታ እንቅፋት ሆኖ ያጋጥም ይሆን?

“አይ! ደሞዝ ችግር አይሆንም፡፡”

በኦቦምያንግ ዙሪያስ 

“አይ ስለሱ ምንም የምለው ነገር የለም፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ጥሩ የሚሆነው ሚስጥር ሲሆን ነው፡፡ 

“ነገሩ ከጫፍ ሲደርስ ይፋ ታደርገዋለህ፡፡ ከሳንቼዝ ውጪ ምንም ለስኬት የቀረበ ነገር የለም፡፡”

ኦዚል በመጪው ጊዜ አርሰናል ይቆያል?

“አዎ!”

የጆኒ ኢቫንስ ዝውውር ጉዳይስ እንዴት ነው?

“በእዛ ዙሪያ ምንም የምናገረው ነገር የለም”

ሳንቼዝን ባሳለፍነው ክረምት ባለመሸጦ ይፀፀታሉ?

“ተመልከት! ችግሩ አሁን እንዳለው ተመሳሳይ ነበር፡፡ እሱን ልሸጠው የምችለው የእሱን ምትክ ማግኘት ስችል ነው፡፡ 

“ባሳለፍነው ክረምት ልሸጠው እችል ነበር፡፡ ነገርግን ምትክ ማግኘት ባለመቻሌ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ”

በተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) ዳኝነት ዙሪያ 

“የምትፈልገው አሰራሩን ማዘመን ነው፡፡ በዚህ መሀከል ግን ትንሽ ችግር መፈጠሩ አይቀርም፡፡ በግሌ እኔ የአሰራሩ ደጋፊ ስሆን በቴክኖሎጂ ወደፊት መሄድ እንዳለብንም አምናለሁ፡፡ …” 

በቅዳሜ ጨዋታ ዙሪያ 

“ባሳለፍነው ታህሳስ እስክንገጥማቸው እና እስክናሸንፋቸው ድረስ ፓላሶች በጥሩ ጉዞ ላይ ነበሩ፡፡ እኛ ጨዋታውን ለማሸነፍ የምንፈልገው ነገር በራሳችን ብቃት ላይ ማተኮር ነው፡፡ 

የ 2018 ከባድ አጀማማርና ያሳለፍነው አመት የአርሰናል የወረደ ብቃት?

“አይ ከ 2018 መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ነገሩ ጥሩ አይደለም፡፡ አስፈላጊው ጉዳይ ቡድኑ ለነገሮች ምን መልስ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡ ይህንን አስካውቅ ድረስም በቡድኑ ረጅም ጊዜ እቆያለሁ፡፡

 “ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች አሉ፡፡ ነገርግን አሁን ያለው ነገር አስደናቂ ነው፡፡ በቀጣይ ወደቻምፒዮንስ ሊጉ የምንመለስ ሲሆን ኢሮፓ ሊግም ሌላው ኢላማችን ነው፡፡”

በጭንቀት ዙሪያ 

“የጭንቀት መለከያ የለኝም፡፡ ነገርግን ጭንቀት ካለብህ ከሜዳ ውጪም ማታ ላይም ወጣጥሮ ይይዝሀል፡፡ እኔ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን መቋቋም የምችል ስሆን ያለኝ ልምድም ትኩረት እንዳደርግ ይረዳኛል፡፡”

ሳንቼዝ የ 500,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ በዩናይትድ ሊከፈለው እንደሆነ በመነገሩ ዙሪያ

“እነሱ ለሳንቼዝ ባቀረቡት ገንዘብ ዙሪያ አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ማንችስተር ዩናይትዶች ባላቸው ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ምክንያት ለተጫዋቾቻቸው የሚከፍሉትን ገንዘብ ስለሚያሳድጉ ለእነሱ ክብር አለኝ። የሚከፍሉት ገንዘብ የእነሱ ጉዳይ ነው። 

“ዩናይትድ በገንዘብ ደረጃ በትልቅ አቅም ላይ የሚገኝ ነው። ስለዚህ እነሱ በሚከፍሉት ዙሪያ ችግር የለብኝም።” 

በዊልሻየር ዝውውር ዙሪያ 

“እኛ የምንፈልገውን እናውቃለን፡፡ እሱ በዚህ እንዲቆይ እንፈልጋለን፡፡ እሱም መቆየት ይፈልጋል፡፡ እኛ የሚያረካ የገንዘብ ስምምነት እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡ አሁን እየሞከርን ያለነውም ያንን ለማሳካት ነው፡፡”

አርሰናል ሌሎቹን ቡድኖች መቀናቀን አይችልም ማለት ነው?

“በገንዘብ ደረጃ አዎ፡፡ ነገርግን ያ ማለት በሜዳ ላይ ሌሎችን አንፎካካርም ማለት አይደለም። ዩናይትድና ሲቲ ከእኛ የበለጠ አቅም እንዳላቸው የሚደበቅ ነገር አይደለም፡፡”

አርሰናል ለሳንቼዝ ምን ያህል ዋጋ አቀረበ?

“እኛ ማቅረብ የምንለውን ያህል አቅርበንለት ነበር፡፡ ምንአልባት አንድ ቀን ቁጥሩን እናገረው ይሆናል፡፡”

Advertisements