የዕለተ ሀሙስ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች 

የእንግሊዝ፣ የስፔን፣ የጣሊያን፣ የጀርመን እና የፈረንሳይ የጥር ወር የዝውውር መስኮት አሁንም እውን የሆኑ አዳዲስ ዝውውሮችን እና በቀጣዮቹ ቀሪ የዝውውር ቀናት እውን ሊሆኑ የሚችሉ የዝውውር ጭምጭምታዎችን ማሰማቱን ቀጥሏል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም በዕለቱ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውር ትኩረት የሆኑ አጫጭር የዝውውር ወሬዎችን እንደሚከተለው መራርጣ እንደሚከተለው ወደእናንተ ብላለች።

ስፔን

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የክርስቲያኖ ሮናልዶ እና የዚነዲን ዚዳን ምትክ ይሆኗቸው ዘንድ የቶተንሃሞቹን ሃሪ ኬን እና ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን በእቅዳቸው ውስጥ ማስገባታቸውን የላ ፖርቴራ ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል።

ኻመስ ሮድሪጌዝ ወደሪያል ማድሪድ የመመለሱን ጉዳይ ጨርሶ እንዳልተወው የዘገበው ማርካ ጋዜጣ ነው። 

ጋዜጣው በዘገባው ኮሎምቢያዊው ተጫዋች በባየር ሙኒክ እስከ2019 ክረምት ድረስ የሚያቆየው የውል ስምምነት እንዳለው እና የቡንደስሊጋው ክለብ ተጫዋቹን የመግዛት አማራጭ ያለው ቢሆንም ስምምነቱ ግን አስገዳጅ እንዳልሆነ። ዚነዲን ዚዳን ክለቡን የሚለቅ ከሆነ ግን ተጫዋቹ ወደስፔን ለመመለስ ፍላጎት ሊኖረው እንደሚችል ሆኖም ፈረንሳዊው አሰልጣኝ የሚቆይ ከሆነ ግን በማድሪድ ቦታ እንደማይኖረው አክሎ ገልፅዋል።

ሊቫንቴ በሎይች ሬሚ ላይ ፍላጎት አሳድሯል። 

ፈረንሳዊው ተጫዋች ከቼልሲ ላስ ፓልማስን የተቀላቀለው በዚህ ክረምት የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ ግን ወደላ ሊጋው ተቀናቃኙ ሊመለስ እንደሚችል ሱፐርዲፖርቶ ጋዜጣ ዘግቧል።

ፈረንሳይ

ላሳና ዲየራ የማንችስተር ዩናይትድን ጥያቄ ውድቅ አድጎ ለፒኤስጂ እንደሚፈርም ላ ፓሪሲየን ጋዜጣ ዘግቧል።

 አማካኙ በሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ያሰለጠኑት ጆሴ ሞሪንሆ ዝውውሩ ላይ ተሳታፊ ከመሆናቸው በፊት የሊግ ዋኑን ክለብ ለመቀላቀል ተዘጋጅቷል። የ33 ዓመቱ ተጫዋች ሲጫወትበት ከነበረው አል ጃዚራ ክለብ ጋር ያለው ኮንትራት የተጠናቀቀ ቢሆንም ወደእንግሊዝ ከመመለስ ይልቅ ወደፓሪስ መመለስን ምርጫው አድርጓል።

ሉካስ ሞራ የቶተንሃም የዝውውር ዒላማ ውስጥ ገብቷል። 

የለኪፕ ጋዜጣ ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ ፓቸቲኖ የአጥቂ ክፍል አማራጫቸውን ለማጠናከር ሲሉ በፒኤስጂ ተፈላጊነቱ የቀነሰውን ብራዚላዊውን ተጫዋች ሁነኛ እቅዳቸው አድርገውታል። ይሁን እንጂ ስፐርሶች ተጫዋቹን በውሰት ለመውሰድ የሚፈልጉ በመሆናቸው ሁለቱ ክለቦች ወደስምምነት መቅረብ አልቻሉም። ፒኤስጂዎች በሚዛናዊ የፋይናንስ ደንብ ገደብ ምክኒያት ፍላጎታቸው ሉካስን በቋሚነት መሸጥ ነው።

ጀርመን

ቦሩሲያ ዶርትሙንዶች የአርሰናል የዝውውር ዒላማ ለሆነው ፒየር-ኤመሪል አውባምያንግ የዝውውር ጥያቄ 61.7 ሚ.ፓ እንዲቀርብላቸው ይፈልጋሉ።

ጋቦናዊው ተጫዋች ክለቡን የሚለቅ ከሆነም የጀርመኑ ክለብ የመድፈኞቹ የፊት ተጫዋች ኦሊቪየ ዥሩ ምትክ እንዲሆናቸውም ማሰባቸውንም የኪከር ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል።

ጣሊያን

እንደቱቶ መርካቶ ዘገባ ጁቬንቱሶች በክረምቱ የአርሰናሉን ተከላካይ ሄክቶር ቤለሪንን ለማስፈረም ውጥን ይዘዋል። 

የሴሪ አው ሻምፒዮን የ22 ዓመቱን ስፔናዊውን ተጫዋች ከ2014 አንስቶ ሲከታተለው ቆይቷል።

የቶሪኖው አጥቂ አንድሪያ ቤሎቲ የኤሲ ሚላን የፊት መስመር ህልም መሆኑን ኮሪየር ዴሎ ስፖርት ጋዜጣ ዘግቧል። 

የአንድሬ ሲልቫ ዝውውር ባለመሳካቱ ሮዞነሪዎቹ በክረምቱ ቤሎቲን ለማዛወር እንቅስቃሴ የሚጀምሩ ይሆናል።

ዳንኤል ስተሪጅ ወደጣሊያን ለማራት ተቃርቧል። 

ሊቨርፑል እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በኢንተር ሚላን በውሰት እንዲቆይ አጥቂውን ለዝውውር ስምምነት ማቅረቡን የዘገበው ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ነው።

እንግሊዝ

daily express

 • የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ጋርዝ ቤል ወደማንችስተር ዩናይትድ ለማምራት መንገድ ላይ እንደሚገኝ ለክለቡ ማሳወቁ ተዘግቧል።
 • ጁቬንቱስ የአርሰናሉን ተከላካይ ሄክቶር ቤለሪንን ለማስፈረም ድርድር ጀምሯል።

daily mirror

 • አንዲ ካሮል ባቼልሲ እየተፈለገ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ልምምድ መስራት እንደማይችል ለክለቡ የተናገረ ቢሆንም፣ በቁርጭምጭሚቱ ላይ የተደረገለት የህክምና ምርመራ ግን ምንም ያመላከተው ችግር የለም። 
 • የኒውካሰሉ አማካኝ ሄነሪ ሳቬት በ5 ሚ.ፓ ወደሞንፔሌ እንዲዛወር ለሽያጭ ቀርቧል።

daily telegraph

 • ማንችስተር ዩናይትድ፣ ከሪያል ማድሪድ በኩል ያለው ፍላጎት ለመግታት ሲል ከዴቪድ ደ ኽያ ጋር ስለረጅም ጊዜ ቆይታ የኮንትራት ስምምነት መነጋገር ጀምሯል።
 • ዳኒኤል ስተሪጅ የሲቪያና እና የኢንተር ሚላንን ትኩረት ስቧል።
 • ዌስት ሃም አንዲ ካሮልን ለቼልሲ ለመሸጥ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ በማንኛውም የዝውውር ስምምነት ግን ሚቺ ባትሹአዪን ማግኘት ፈልጓል።

the sun

 • አሌክሲ ሳንቼዝ ማንችስተር ዩናይትድን በ118.3 ሚ.ፓ ዋጋ ስምምነት ለመቀላቀል ከተስማማ በኋላ በበብሪታኒያ 500,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ የሚያገኝ የመጀመሪያው ተጫዋች ሊሆን ነው።
 • የፒየር-ኤመሪክ አቡመያንግ ወኪል እና አባት የሆኑት ፒየር-ፍራንኮይስ ተጫዋቹ በ53 ሚ.ፓ ወደአርሰናል የሚያደረገውን ስምምነት ለማጠናቀቅ ወደለንደን በረዋል።
 • ዌት ሃሞች በሳምንት 100,000 ፐውንድ ደመወዝ ተከፈይ የሆነውን አንዲ ካርልን ቼልሲዎች ለመውሠድ ማሰባቸው “ስድብ” እንደሆነ ተናግረዋል።
 • ማንችስተር ዩናይትዶች የዌስት ብሮሙን ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስን ዝውውር ለማጠናቀቅ 23.5 ሚ.ፓ ፈሰስ ሊያደረጉ ነው።
 • ራፋ ቤኒቴዝ የወደፊት እጣ ፈንታቸው በኒውካሰል እንዲሆን የሚያጤኑበት ቢሆንም ከመጪው ክረምት በፊት ግን ውሳኔ ላይ አይደርሱም። 
 • ሊቨርፑሎች ቤን ዉድበርንን የቀድሞ የዌልስ አሰልጣኙን፣ ክሪስ ኮልማንን በሰንደርላንድ በውሰት እንዲቀላቀል ማድረግን ፈቀደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል።
 • ኸደርስፊልዶች የቬቮውን ቤልጂየማዊ አማካኝ ሳሙኤል ባስቲየንን በ3.5 ሚ.ፓ ሊያዛውሩ ነው።

daily star

 • ዋትፎርዶች 29 ሚ.ፓ ዋጋ የተተመነውን የሌስተር አጥቂ ኢስላም ስሊማኒን ዝውውር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ንግግር ያደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 • ማንችስተር ሲቲዎች የሪያል ሶሴዳዱን ተከላካይ ኢኒጎ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ጥረታቸውን ይገፉበታል።
 • ጭንቀት የገባቸው የኒውካሰል ደጋፊዎች ለክለቡ ጥቅም ሲሉ ባለቤቱ ማይክ አሽሊ ክለቡን እንዲሸጡ እየወተወቱ ነው።
 • የዋትፎርዱ አጥቂ ስቴፋኖ ኦካካ ወደማርሴ የሚያደረገውን ዝውውር ሊያጠናቅቅ ነው።

daily mail

 • ሊቨርፑል እስከውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ ዳንኤል ስተሪጅን በውሰት ለመውሰድ ከሲቪያ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
 • ስዋንሲዎች ከፖርቶ ከተዛወረበት ጊዜ አንስቶ ብቃቱን ማሣየት የቸገረውን የኤሲ ሚላኑን አጥቂ አንድሬ ሲልቫን እየተከታተሉት ነው።
 • ቶተንሃሞች በሴሪ አው ክለብ ለሚፈለገው ክርስቲያን ኤሪክሰን አዲስ የኮንትራት ስምምነት ሊያቀርቡለት ነው። ዴንማርካዊ ተጫዋች ከክለቡ ጋር ቀሪ ሁለት ዓመታት የኮንትራት ስምምነት አለው።
 • ሪቻርልሰን በዋትፎርድ ያለውን የወደፊት ቆይታ በክረምቱ የሚያጤንበት ቢሆንም እንኳ ክለቡ ተጫዋቹን በጥር ወር የመሸጥ ፍላጎት የለውም።
 • ጆን ፍላናገን ረቡዕ ዕለት የ12 ወራት አስገዳጅ የማህበረሰብ አገልጋሎት እንዲሰጥ ከተፈረደበት በኋላ በሊቨርፑል የሚኖረው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከባድ አደጋ ውስጥ ገብቷል። 

the times

 • ፊል ኔቭል የእንግሊዝ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ከተሾመ በኋላ ካሲ ስቶኒይ የቡድኑን የአሰልጣኞች ክፍሉን ሊቀላቀሉ ነው። 
Advertisements