ዶርትሙንዶች በአርሰን ቬንገር “አክብሮትየለሽ” ንግግር ቅር መሰኘታቸውን ገለፁ

ቦሩሲያ ዶርትሙንዶች አርሰን ቬንገር የአርሴናል የዝውውር ዒላማ የሆነው ፒየር-ኤመሪክ ኦውባምያንግ ለክለቡ ተስማሚ ስለመሆኑ የሰጡትን አስተያየት “አክብሮትየለሽ” እንደሆነ በመግለፅ በጉዳዩ ላይ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

መድፈኞቹ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል የተቃረበውን አሌክሲ ሳንቼዝ ምትክ በማግኘት ክለባቸውን ለማጠናከር ሲሉ ሂነሪክር ሚኪታሪያንን ባተቃራኒው ወደክለባቸው ለማዛወር ወደዝውውር ገበያው ገብተዋል። ነገር ግን ቬንገር ከዚህም ባለፈ ክለባቸውን ማጠናከር ይሻሉ። ለዚህ ደግሞ የዝውውር ዒላማቸው ውስጥ የሚገኘው ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ ነው።

ዛሬ ስለክለባቸው ወቅታዊ የዝውውር እንቅስቃሴ ለቀረበላቸው ጥያቄ በጋቦናዊው የፊት ተጫዋች ላይ ፍላጎት ያላቸው ስለመሆን ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው ቬንገር ዝውውሩ ይፋ እስኪሆን ድረስ “ሚስጥር” መሆኑን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አውባምያምግ ለአርሰናል የሚመጥን ባህሪ ያለው ተጫዋች ስለመሆኑ ለቀረባቸው ጥያቄ ቬንገር “አዎ። ምክኒያቱም ባህሪ  በጣም አዎንታዊም ሆነ በጣም አሉታዊም ሊሆን ይችላል። በአጠቃላይ የምትመለከተው የተጫዋቹን የእግርኳስ [ህይወት] ስኬት ነው።” በማለት ተናግረው ነበር።

ይህን ንግግራቸውን ተከትሎም ዶርትሙንዶች በክለቡ ደጃፍ ላይ በሚገኘው የ28 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር ጉዳይ በሁለቱ ክለቦች በኩል ምንም አይነት “ግንኙነት አለመደረጉን” በመግለፅ የቬንገርን ንግግር “አክብሮትየለሽ” ሲሉ ገልፀውታል።

–>

Advertisements