ፊፋ የሃገራት ደረጃ / ጀርመን በመሪነቷ ስትቀጥል ኢትዮጵያ 137ኛ ሆናለች

ወርሃዊው የፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ ዛሬ ይፋ ሲሆን ከአንድ እስከ 10 የሚገኙ ሃገራት ምንም አይነት የደረጃ ለውጥ ሳያስመዘግቡ ቀጥለዋል፡፡

የዓለም ሻምፒዮኗ ጀርመን መሪነቷን አስጠብቃ መቀጠል የቻለች ሲሆን በቀጣዩ ክረምት በሚደረገው የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ትኩረትን ከሳቡ ሃገራት አንዷ የሆነችው ብራዚል በሁለተኝነት ትከተላታለች፡፡

የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ፖርቱጋል በሶስተኝነት ስትገኝ አርጀንቲና ፣ ቤልጅየምና ስፔን በተከታታይ ከአራት እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ተቆናጠዋል ፤ ፓላንድ ፣ ሲውዘርላንድ ፈረንሳይና ቺሊ ከ ሰባት እስከ አስር ያለውን ደረጃ የያዙ ሃገራት ናቸው፡፡

ከአፍሪካ መሪነቱን የያዘችው የሰሜን አፍሪካዋ ቱኒዚያ ስትሆን ከዓለም ደግሞ 23ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ ቱኒዝያን ተከትለው ሴኔጋልና ግብፅ በሁለተኝነትና በሶስተኝነት አህጉራቸውን ይመራሉ፡፡

ኢትዮጵያ ስድስት ደረጃዎችን በማሻሻል ባለፈው ወር ከነበረችበት 143ኝነት ወደ 137ኝነት ተጠግታለች፡፡

የፊፋ ሃገራት የደረጃ አወጣጥ መስፈርት ብዙ ጊዜ አወዛጋቢና አስገራሚ በመሆን ስሙ ይነሳል፡፡

Advertisements