Skip to content
Advertisements

ባየርን ሙኒክ ጀርመናዊውን ኮከብ ከታላላቅ ክለቦች በመንጠቅ የግሉ አደረገ


ማንችስተር ዩናይትድን ጨምሮ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ጀርመናዊው ወጣት ኮከብ ሊዮን ጎሬትዝካ የባቫሪያኑ ክለብ ተጫዋች ለመሆን እንደተስማማ የሻልካው አሰልጣኝ ክርስቲያን ሄደል በቁጭት ገልፀዋል፡፡

በመጪው ክረምት የኮንትራት ውሉ የሚጠናቀቀው ተጫዋች በሻልካ 04 እንዲቆይ ክለቡ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም ተጫዋቹ ጥያቄውን አሻፈረኝ በማለት ለአገሪቱ ታላቅ ክለብ መጫወት የሚያስችለውን ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡
የሻልክ አሰልጣኝ የሆኑት ሄደል እንደተናገሩት “ጎሬትዝካን ለማጣት መገደዳችንን ስገልፅ በቁጭት ነው ፤ ትናንት የሙኒክ ስራ አስፈፃሚ ካርል ሄይንዝ ሩሚኒገ ከተጫዋቹ ጋር መስማማታቸውንና የጤና ምርመራውን ጭምር ማጠናቀቃቸውን አሳውቀውናል፡፡በጣም አስፈላጊ የሆነውን ተጫዋቻችንን ማጣታችን ነው” ብለዋል፡፡

አሰልጣኙ ጨምረውም “ተጫዋቹን ለማቆየት ብዙ ጥረት አድርገናል ፤ ሆኖም ከቀጣዩ ሐምሌ ጀምሮ የባየርን ተጫዋች መሆንን መርጧል” በማለት አጠቃለዋል፡፡
የ22 አመቱ ኮከብ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን 12 ጨዋታዎችን አድርጎ 6 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በቦኸም አካዳሚ አድጎ በ2013 ሻልክን መቀላቀል ከቻለ በኋላ ለክለቡ ከ 100 በላይ የሊግ ተሳትፎን ማሳካት ችሏል፡፡

Advertisements

ዘውዱ በሬሳ View All

ዘውዱ በሬሳ የኢትዮአዲስ ስፖርት ድረ-ገፅ የስፖርት ፀኃፊና ኤዲተር ነው፡፡

%d bloggers like this: