ስንብት / ዋትፎርድ ከክለቡ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ጋር መለያየቱን አሳወቀ

ከክሪስማርስ በአል በፊት ባለፈው ህዳር ወር ላይ ስማቸው ከኤቨርተን ጋር ተያይዞ የነበረው ፖርቹጋላዊው ማርኮ ሲልቫ ከዋትፎርድ ሀላፊነተቻው በይፋ ተነስተዋል።

ኤቨርተን ሮናልድ ኩማንን ካሰነበተ በኋላ ተተኪ አሰልጣኝ አድርጎ ለመቅጠር ካሰባቸው አሰልጣኞች መካከል የዋትፎርዱ ማርኮ ሲልቫ ይገኙበት ነበር።

ነገርግን ክለቡ ለአሰልጣኙ ፈቃድ ባለመስጠቱ ማርኮ ሲልቫ ወደ ጉዲሰን ፓርክ ሊያደርጉት የነበረው ዝውውር ሳይሳካ ቀርቷል።

አሰልጣኙ ኤቨርተኖች ከፈለጓቸው በኋላ ያደረጓቸው 13 ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻሉት በሶስቱ ብቻ ሲሆን ከወራጅ ቀጠና በአምስት ነጥብ ርቀው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ በአስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው የክለቡ ባለስልጣናትን አላስደሰተም።

ትናንትናም በሌሲስተር 2-0 የተሸነፉ ሲሆን ይህም የአሰልጣኙ የክለቡ ቆይታ ፍፃሜ ሆኗል።

ክለቡ በመግለጫው ባለፈው ክረምት ማርኮ ሲልቫን መቅጠሩ ትክክለኛ ውሳኔ እንደነበር ጠቅሶ ነገርግን አሰልጣኙ ወደ ሌላ ቡድን ለማቅናት ያደረጉት ያልተገባ ግኑኘነት ደስተኛ እንዳላደረገቸው በመግለፅ ለስንብቱ ምክንያት እንዳደረጉት አሳውቀዋል።

ክለቡ በምትካቸውም በቅርቡ ሌላ አሰልጣኝ እንደሚተኩ እስከዛው ድረስ ግን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ አስተያየቶችን ከመስጠት እንደሚቆጠቡ አሳውቋል።

አሰልጣኙ በፕሪምየርሊጉ በውድድር አመቱ የተሰናበቱ ስምንተኛው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ክለቡ አመሻሹ ላይ የቀድሞ የሩቢን ካዛን አሰልጣኝ የነበሩት ሀቪ ጋርሺያን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ለ 18 ወራት መቅጠሩን አሳውቋል።

Advertisements