ሩሲያ / የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ሚስቶቻቸውን ወይም እጮኞቻቸውን ወደአለም ዋንጫው ይዘው እንዲጓዙ ተፈቀደላቸው

የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለ 2018 የሩሲያ አለም ዋንጫ ሚስቶቻቸውን ወይም እጮኞቻቸውን ወደ ውድድሩ ስፍራ ይዘው እንዲጓዙ ተፈቅዶላቸዋል።

ይህን ውሳኔ ያሳለፉት የንስሮቹ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህ ውሳኔው በአዕምሮ ደረጃ ተጫዋቾቹን እንደሚረዳቸው ገልፀው በውድድሩ ላይ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይም ትኩረት እንዲያደርጉ ትልቅ እገዛ እንዳለውም አስረድተዋል።

ባሳለፍነው አመት የናይጄሪያው አምበል ሚካኤል ኦቢ ናይጄሪያ ለአለም ዋንጫ የማታልፍ ከሆነ የሚስቱ ቤተሰቦች እንደሚገሉት በቀልድ መልክ መናገሩ አይረሳም።

Advertisements