የዕለተ ሰኞ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

ሊጠናቀቅ ስምንት ቀናት በቀሩት የአውሮፓ የጥር ወር መስኮት የሚጠበቁ ትልልቅ ዝውውሮች ይከናወኑበታል ተብሎ ይተሰባል። ኢትዮአዲስ ስፖርትም አበይት ያለቻቸውን አጫጭር የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውር ወሬዎችን እንደሚከተለው አሰናድታለች።


አሌክሲስ የህክምና ምርመራ ማለፉን ተከትሎ በዩናይትድ መለያ ታይቷል


አሌክሲስ ሳንቼዝ በዩናይትድ የተደረገለትን የህክምና ምርመራ ማጠናቀቁን በማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ ከተዘገበ በኋላ የማንችስተር ዩናይትድን መለያ ለብሶ የሚያሳይ ምስል ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ በትዊተር ማህበራዊ ገፅ ላይ ተለቋል።


ማታ በዩናይትድ ደስተኛ ነው


ኹዋን ማታ በማንችስተር ዩናይትድ ደስተኛ ሲሆን፣ በውድድር ዘመኑ መጨረሻም ክለቡን የመልቀቅ ዕቅድ እንደሌለው የስፔኑ ሱፐርዴፓርቴ ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል።


ዥሩ የኦባምያንግ ስምምነት አካል በመሆን ዶርትሙንድ ይቀላቀላል


ፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ ወደአርሰናል የሚያደረገውን ዝውውር የሚያጠናቅቅ ከሆነ ፈረንሳያዊው የመድፈኞቹ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ የዝውውሩ አካል በመሆን እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ዶርትሙንድን በውሰት የሚቀላቀል መሆኑን የጀርመኑ ጋዜጣ ኪከር ዘግቧል።


የአርሰናል የዝውውር ዒለማ የሆነ ፓቨን ለዝውውር ረሱን አዘጋጅቷል


Cristian Pavon Boca Juniors

ክርስቲያን ፓቫን በቦካ ጁኒየርስ ያለው የወደፊት ቆይታ ሊያበቃ እንደሚችል ማመኑን ተከትሎ 37 ሚ.ዩሮ በሚሆን የዝውውር ዋጋ ወደአርሰናል ለመዛወር በሩን ክፍት አድርጓል። ታጫዋቹ በቦካ እስከ2022 ድረስ የሚያቆየው የኮንትራት ስምምነት ያለው ሲሆን፣ የውል ማፍረሻውም 37 ሚ.ዩሮ ነው።


ፓቸቲኖ የማልኮምን ወሬ አስተባበሉ


Malcom Bordeaux

ማውሪሲዮ ፓቸቲኖ ቶተንሃም የቦርዶውን የክንፍ ተጫዋች ማልኮምን ከሰሜን ለንደን ተቀናቃኙ አርሰናል በልጦ ሊያስፈርም እንደሆነ የተዘገበውን ወሬ አጣጥለዋል።


ሪያል ማድሪድ ወደደኽያ ፍላጎቱ ሊመለስ ይችላል 


David de Gea Manchester United

የአትሌቲክ ቢልባዎች ግብ ጠባቂ ኬፓ  አሪዛባላጋ ከሪያል ማድሪድ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ተከተሎ የ ላ ሊጋው ክለብ ሌላ የግብ ጠባቂ ፍለጋውን ሊቀጥል ይችል ይሆናል በሚል ማንችስተር ዩናይትድ ስጋት እንደገባው የ ዘሚረር ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል። ደ ኽያ በዩናይትድ አሁን ያለውን ኮንትራት ለተጨማሪ በአንድ ዓመት ለማራዛም ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል። 


ሮናልዶ ዩናይትድን ለመቀላቀል ክፍያውን ሊቀንስ ይችላል


Cristiano Ronaldo Real Madrid Deportivo

አንደ ስፔኑ ዶን ባሎን ዘገባ ከሆነ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሪያል ማድሪድ መውጣት የሚችልበትን መንገድ ለማመቻቸት ሲል ደመወዙን ዝቅ ለማድረግ ራሱን ሊያዘጋጅ ይችላል። ፓርቱጋላዊው ተጫዋች ወደማንችስተር ዩናይትድ የመመለስ ፍላጎት እንዳለው ዘገባዎች አመልክተዋል።

daily star

 • ማንችስተር ዩናይትድ የሪያል ማድሪዱን ኮከብ ጋርዝ ቤልን ለማስፈረም ከበርካታ ክለቦች ፉክክር ገጥሞታል።

daily express

 • የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ በዚህ የውድድር ዘመን ከሊጉ የመውረድ አደጋ የሚኖርበት ዕድል ሊኖር እንደሚችል አምነዋል። 

the guardian

 • አርሰን ቬንገር ያለተረጋገጠው የአሌክሲ ሳንቼዝ የወደፊት ቆይታ የቡድናቸውን ሞራል እንደጎዳው ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
 • ሳም አላርዳይስ ዋይኒ ሩኒ እና ጊይልፍ ሲጉርድሰን በፍጥነት ማነስ ምክኒያት በአንድ ቡድን ውስጥ ሊጫወቱ እንደማይችሉ ገልፀዋል።

daily mirror

 • ዳንኤል ስተሪጅ የቀዮቹ አሰልጣኝ በውሰት ለመዛወር የሚችልበትን ዕድል ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ሲቪያን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ለሊቨርፑል ተናግሯል።
 • አርሰን ቬንገር አሌክሲ ሳንቼዝ ወደማንችስተር የሚያደረገው ዝውውር በገንዘብ ምክኒያት እንደሆነ ገልፀዋል።
 • ኤቨርተን፣ ኒውካሰል እና ብራይተን ለብሪስቶሉ የግራ መስመር ተከላካይ ጆ ብርያን 7 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ አቅርበዋል።
 • ፓል ኢንስ ማንችስተር ዩናይትድ አሌክሲ ሳንቼዝን ማስፈረሙ ከማንችስተር ሲቲ “በብዙ ማይልሶች እንደሚገዝፍ” የሚያስመሰክር መሆኑ ገልፅዋል።

daily telegraph

 • ራፋኤል ቤኒቴዝ ከጥር ወር ማጠናቀቅ በፊት ስለኮንትራት እንደማይነጋገሩ ለኒውካሰል ተናግረዋል።
 • አርሰናሎች የአሌክሲስ ሳንቼዝ በሄነሪክ ሚኪታሪያን የሚደረገው የቅይይር ዝውውር ለመሳካት መቃረቡን ተከትሎ አሁን ትኩረታቸው ፒየር-ኤመሪክ ኦባምያንግ ወደማምጣት ዞሯል። 
 • ስዋንሲዎች አንድሬ አየውን በ14 ሚ.ፓ ዳግም ለማስፈረም የሚያደረጉት ጥረት በዌስት ሃሞች ውድቅ ከተደረገ በኋላ ለዳግመኛ ጥያቄ የክለባቸውን የዝውውር ክብረወሰን ሊሰብሩ ነው።

the independent

 • ምንም እንኳ የስቶክ ሲቲው አሰልጣኝ ፓል ላምባርት ፒተር ክራውች የማይሸጥ ተጫዋች እንደሆነ ቢገልፁም ቼልሲ ግን አሁንም ተጫዋቹን ሊያስፈርም ይችላል።

the sun

 • ኬቨን ደ ብሩይን በማንችስተር ሱቲ ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ የኮንትራት ስምምነት ለመፈረም ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ስምምነቱም ዛሬ (ሰኞ) ይፈ ሊሆን ይችላል።
 • ቫር (በቪዲዮ የታገዘ ዳኘነት) በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ላይ በፊፋ በይፋ ተግራባራዊ ይሆናል።
 • የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ የሊሉን የመኃል ተከላካይ ሳዳማ ሶመአሬን ለማፈረም እየተከታተሉት ነው።
 • የአርሰናል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑ ኢቫን ጋዚዲስ የፒየር-ኤመሪክ ኦውባምያንግን የዝውውር ስምምነት ለማጠናቀቅ በዶርትሙንድ ይገኛሉ። 

the times

 • የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አልጣኙ ስቲቭ ማክላረን በተቻላቸው ፍጥነት ወደአሰልጣኝነት ስራ መመለስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

daily record

 • ሰንደርላንዶች የሬንጀርሱን ዴቪድ ባቴስን ለማዛወር ተዘጋጅተዋል።
Advertisements