ይፋዊ/ ብራዚላዊው ሮቢንሆ ለቱርኩ ክለብ ሲቫስፖር ፊርማውን ለማኖር ተስማምቷል  

Image result for Robinho

በ2013 በጣሊያኑ ኤስ ሚላን ሳለ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ባሳለፍነው ህዳር  ወር የ9 አመት እስራት በጣሊያን ፍርድ ቤት የተወሰነበት የ33 አመቱ የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ኮከብ ሮቢንሆ ለቱርኩ ክለብ ሲቫስፖር ለመጫወት መስማማቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከብራዚሊ ክለብ አትሌቲኮ ሚኒሪዮ ጋር በያዝነው አመት መጀመሪያ የተለያየው ሮቢንሆ  ወደ ቱርኩ ክለብ ማቅናቱን ሲቫስፖር በይፋ ያሳወቀ ሲሆን ከቀናት በኋልም በይፋ የቱርክ ሱፐር ሊግን እንደሚቀላቀል ግልጽ አድርጓል፡፡

በጣሊያኑ ክለብ ኤስ ሚላን ከ2010 እስከ 2014 ድረስ በቆየበት ወቅት በ2013 የ22 አመት እድሜ ያላትን እንስት ከ5 ጓደኞቹ ጋር በመሆን ደፍሯል በሚል የ9 አመታት ፍርድ የተፈረደበት ሮቢንሆ ወደ ቱርክ የሚያደርገው ዝውውር በጸናበት የእስር ትህዛዝ ምክንያት እክል የማይገጥመው ሲሆን ሮቢንሆ የእስር ትህዛዝ ሊወጣበት የሚችለው በጣሊያን ከተማ ከተገኘ እንደሆነ ብቻ የተደነገገ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በተለያዩ ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ላይ መንቀሳቀስ እና መስራት የሚችል ይሆናል፡፡

የስፔን ላሊጋን ከሪያል ማድሪድ ጋር እንዲሁም የጣሊያን ሴሪያን ከኢነተር ሚላን ጋር እና የቻይና ሱፐር ሊግ ዋንጫ ከጉዋንዙ ኤቨርግራንዙ ጋር መሳም የቻለው ብራዚላዊው ኮከብ በተጫዋችነት ዘመኑ እስካሁን 695 ጨዋታዎች አድርጎ 233 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

Advertisements