ድርድር/ የአርሰናል ባለስልጣናት በፔር ኤምሪክ ኦቦሚያንግ ዝውውር ጉዳይ ለማውራት ወደ ጀርመን አቅንተዋል

Borussia Dortmund have confirmed Arsenal have made an enquiry for the Gabon international

የ2016/2017 ከፍተኛ ግብ አግቢያቸውን በማንችስተር ዩናይትድ የተነጠቁት መድፈኞቹ ምንም እንኳ አርሜንያዊውን ኮከብ ሄነሪክ ሜኬቴሪያንን በነጻ ዝውውር ከቀያይ ሰይጣኖቹ ቢያገኙም በጥሩ የዝውውር መስኮት ጋቦናዊውን የቦርሲያ ዶርትመንድ አጥቂ መስመር ተጫዋች ፔር ኤምሪክ ኦቦሚያንግን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም የክለቡ ሊቀ መንበር የሆኑት ኢቫን ጋዚዲስ ጀርመን ማቅናታቸው ተሰምቷል፡፡

ታማኙ ስካይ ስፖርት የውስጥ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንዳወራው ከሆነ አርሰናል እና ቦርሲያ ዶርትመንድ በጋቦናዊው ኢንተርናሽናል ዝውውር ዙሪያ በጠረቤዛ ዙሪያ ድርድር እያደረጉ እንደሆነ የገለጸ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንትም አርሰናል ይፋዊ ያልሆነ የ44 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ጥያቄን ለጀርመኑ ክለብ አቅርቦ እንደነበር እና ቦርሲያ ዶርትመንድም ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን ጋቦናዊው አጥቂ በጥር የዝውውር መስኮት ከመጠናቀቁ በፊት ቦርሲያ ዶርትመንድን መልቀቅ እንደሚልግ ማሳወቁ እና ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በቦርሲያ ዶርትመንድ እና ሄርታ በርሊን መካከል በተደረገው የቡንደስ ሊጋው ጨዋታ ላይ አለመሰለፉ ደግሞ ተጫዋቹ በጥር ወር የጀርመኑን ሀያል ክለብ መልቀቁ አይቀሬነቱን አሳይቷል፡፡

መድፈኞቹ ባሳለፍነው የውድድር አመት በጀርመን ቡንደስ ሊጋ በ31 ግቦች ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ያጠናቀቀውን ተጫዋች ከ50 ሚሊየን ፓውንድ በላይ አውጥተው የሚያስፈርሙት ከሆነ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በክለቡ ክብረወሰን በሆነ ዋጋ ከኦሎምፒክ ሊዮን አርሰናልን በ52 ሚሊየን ፓውንድ የተቀላቀለውን አሌክሳንደር ላካዜቴ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል፡፡

 

Advertisements