ፊፋ በመንግስት የእግርኳስ ጣልቃገብነት ላይ ምን ዓይነት አቋም አለው?

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለቀጣይ የስራ ዘመኑ የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚዎቹን ለማስመረጥ ቀነ ቀጥሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ፊፋ ደረሰኝ ባለው ጥቆማ የምርጫ ደንቦቹ ስለመጣሳቸው በመግለፅ ምርጫው ወደሌላ ጊዜ እንዲራዘም በፃፈው ይፋዊ ደብዳቤ አሳውቋል። ፌዴሬሽኑም የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም ተገዷል። በፊፋ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል “የመንግስት ጣልቃገብነት” ይገኝበታል። ለመሆኑ በፊፋ ዘንድ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ማለት ምን ማለት ነው? በመንግስት ጣልቃ ገብነት ላይስ ፊፋ ምን ዓይነት አቋም አለው?

የፊፋ ድረገፅ እ.ኤ.አ ከ2008 እስከ2016 ድረስ የፊፋ አባል ማህበራት እና የልማት ዳይሬክተር ከነበሩት ቴሪ ሬጌናስ ጋር መንግስታት በእግርኳስ ላይ ስለሚኖራቸው ጣልቃ ገብነቶች እና የእግርኳስ አመራሩ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በ2011 እንደሚከተለው ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር።

ፊፋ ድረገፅ፡ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ማለት ምን ማለት ነው?

ቴሪ ሬጌናስ፡ ፊፋ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የእግርኳስ ማህበራትን በማንኛውም ሁኔታ የመቆጣጠር ስልጣን አለው። ይህ ስልጣን ደግሞ በብሄራዊ ደረጃ የሚገኙ የእግርኳስ ማህበራትን ለመቆጣጠር ከሃገራቱ ማህበራት ውክልና ስልጣን ያለው ነው። ይህም እግር ኳስ እንደጨዋታ እና የጨዋታውን ተቋማት በጠቅላላ ማስተዳደርን፣ መቆጣጠርን እና እና ማልማትን ጭምር ይመለከታል። ማህበራቱም ከማንኛውም የመንግስትም ሆነ የትኛውም አካል ውጪያዊ ጠልቃገብነት ሳይገጥማቸው በነፃነት ይህን የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። በአጠቃላይ የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ማለት መንግስት የቀጥታ ቁጥጥር ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ ማለት ነው።

የተለመደው የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ምንድን ነው?

በጣም የለመዱ የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ጉዳዮች አንድ መንግስት ሆን ብሎ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስራውን በሚገባ እንዳያከናውን እና ውሳኔ እንዳያስልፍ ሲያደርግ ነው። ብዙውን ጊዜ ብሄራዊ ቡድን ባርከታ ጨዋታዎች የሚያመልጡት በመሆኑ የግድ ለውጥ እንዲደረግ ይወስናሉ። እንዲሁም ስልጣኑን የሚረከብ ተገቢውን ሰው ይሾማሉ። ከዚያ ባለፈ ግን በርካታ የተለያዩ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለምሳሌ የመንግስት ተቋሟት ከማህበሩ ውጪ የራሳቸውን ውድድሮች መመስረት ወይም መንግስት አንደኛውን ቡድን ከሌላው በተለየ ለመጥቀም ሲል የሊግ ውጤቶችን የመለወጥ ውሳኔ ማሳለፍ ናቸው።

ይሁን እንጂ እኛ መንግስታትን አንቃረንም። አባል ማህበራቶቻችንም የመንግስታቶቻቸው ተቃራኒ እንዲሆኑ አናበረታታም። በአንፃሩ ከመንግስታት ጋር መልካም ሁኔታ እና ትብብር እንዲመሰረት ያለማቋረጥ ጥረት እናደርጋለን። መንግስት በሃገሩ ላይ ያለውን እግርኳስ የማልማት በጣም ከፍተኛ የሆነ ሚና አለው። በመንግስት እና በብሔራዊ የእግርኳስ ማህበራት መካከል ጥሩ ግንኙነት የሚኖር ከሆነ ደግሞ በጣም ፍሩያማ ውጤት ይኖራል።

ፊፋ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምን ያህል የጣልቃ ገብነት ጉዳዮችን ይመለካታል?

ይህን ያህል ብሎ በቁጥር መግለፅ አስቸጋሪ ነው። “ጉዳይ” ብለህ እንደምትገልፃው ጉዳዮቹም ይለያያሉ። ከአባሎቻቻን ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነት አለን። አንዳንድ ጊዜ ግን ብዥታዎች ይፈጠራሉ። ወይም በሌሎች አካሎቶች ላይ ማስፈራሪያዎች ጭምር ይፈጠራሉ። ነገር ግን እነዚህም ቢሆኑ እንደአንድ አብይ ጉዳይ ላይቆጠሩ ይችላሉ። ምክኒያቱም ገዳዮቹ በአንድ የማብራሪያ መጠየቂያ ደብዳቤ ወይም የቅጣት ማስጠንቀቂያዎች ወዲያውኑ ሊቀረፉ ስለሚችሉ ነው።
ችግሮች ሲፈጠሩ ማህበሩ ችግሩን ከመሰረቱ እንዲገልፅ ይበረታታል። ከዚያም እኛ ለፊፋ ምኑ ላይ ችግር እንደሚሆን እንገልፃልን። እናም ማህበሩ ችግሩን በራሱ እንዲያስተካክል እናበረታታለን።

አንዳድን ጊዜያት ጠልቃ ገብነቱን ለማስቀረት ስንል ከማንግስታት ተወካዮች ጋር ተገናኘን እናነጋገርረለን። ቀጥተኛ ጠልቃጋብነት ከነበረ ብቻ እኛ በጉዳዩ ላይ እንገባለን። እንደዚህ አይናት ጉዳይ ሲኖር ማህበራቱን የሚያግድ የመጨረሻ ቅጠት እንዲተላለፍ ጉዳዩ ለፊፋ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወይም ለአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ይቀርባል። እስከጉባኤ ወቅት ድረስ ማህበሩ በቅጣት ላይ የሚገኝ ከሆነ በፊፋ ምክር ቤት ቅጣቱ ይፋ መሆን አለበት።

ስለዚህ ስለቁጥር ለመናገር በዓመት ከአራት እስከ አስር “ገዳዮች” ሊሆኑ ይችላሉ። በአሁኑ ወቅት (በ2011) የታገደ ማህበር የለም።

ፊፋ ጠንካራ ተቋም ነው። ጥንካሬውም በእግርኳስ ዘርፍ ላይ ብቻ አይደለም።ነገር ግን በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊው ዓለምም ላይ ጭምር ነው። እናም እነዚህን ጥንካሬዎች አባላቶቻችን ለማጠናከር መጠቀም እንችላለንም፤ ይኖርብናልም።

የፊፋ አባል ሃገራት እና የልማት ዳይሬክተር የሆኑት ቴሪ ሬጌናስ

ፊፋ የፓለቲካ ጠልቃ ገብነቶችን እንዴት ይለያል?

በአጠቃላይ የሚያሳውቀን ማህበሩ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ቦታዎች መታገድን ወይም መንግስታቸውን በመፍራት ሊያሳውቁን አይፈልጉም። እንደእግርኳስ አመራር አካል የፓለቲካ ርዕሰ ጉዳዮችን ጨምሮ የዓለም እግርኳስ ሁኔታን ያለማቋረጥ እንቆጣጠራልን። ስለዚህ በፓለቲካው ዓለም ላይ ከሚገኙ፣ በእግርኳሱ ዓለም ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ወይም ሀገር በቀል የሚዲያው ዘርፍ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ልንሰማ እንችላለን። ቀጣዩ እንቅስቃሴያችን ማህበሩ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲያቀርብልን መጠየቅ ነው። ከዚያም ፊፋ ሁኔታውን ለመመርመን ወደስፍራው ተወካዩን ይልካል።

ፊፋ የፓለቲካ ጣልቃ ገብነቶችን ለመግታት ምን አይነት ርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል?

ምንም እንኳ ጠንካራ የትግበራ መርሆዎችና መመሪያዎች ቢኖሩንም በእያንዳንዱን ጉዳይ ላይ መሰረቱን አይተን ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል። ተጨባጭ ውሳኔ ለማሳለፍ ደግሞ ከእገዳ ውሳኔው ባሻገር ሌላ አማራጭ የለንም። ነገር ግን አንድን ማህበር ስታግድ መንግስትን የቱንም ያህል ተፅእኖ በማይፈጥርበት ሁኔታ የፈይናንስ ምንጩንም በማገድ የእግርኳስ ማህበሩን ትቀጣለህ። ስለዚህ የመጀመሪያው እንቅስቃሴያችን ማህበሩ ከመንግስት ጋር ወይም በጉዳዩ ላይ ተሳታፊ ከሆነ አካል ጋር ግንኙነት እንዲያደርግ እና በጉዳዩ ላይ እንዲነጋገር ማበረታት ነው። ይፋዊ በሆኑ ግንኙነቶች አማካኝነት የእግርኳስ ማህበሩ የሚጠብቀውን የቅጣት ክብደትም እናሳውቃለን።
ነገር ግን ከጉዳዩ ውጪ የሆነን ነገር በቁጥጥር፣ በተግባቦት እና አፋጣኝ ውሳኔ ፊፋ የሚፈጠረውን ቀውስ ሊገታ ይችላል። 

ፓለቲካን ከስፖርት/እግርኳስ ጠልቃ ገብነት ለመጠበቅ ፊፋ ከየትኛው ተቋም ጋር በጋር በመሆን በቅርበት ይሰራል?

በመጀመሪያ ደረጃ ከአህጉራት ኮንፌዴሬሽኖች ጋር እንሰራለን። በአንዳንድ ሃገራት በጣም የጋራ የሆኑ ችግሮች ነው ያሉት። ይህም ማለት መንግስታት ጠልቃ ገብ ህጎችን ያወጣሉ፣ እንዲሁም በሁሉም ስፖርቶች ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ። ለምሳሌ የማስተዳዳር ኃለፊነትን ከፌዴሬሽኑ በመንጠቅ ወደመንግስት እጅ ያስገባሉ። በዚህ ምሳሌ መሰርትም እኛ ከዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ግንኙነት እናደርጋለን። ብዙውን ጊዜም የኦሎምፒክ ኮሚቴው በሁሉም ስፖርታች ላይ እንዳለው ውክልና ተባባሪነቱን ያሳየናል።  
ዲሞክራሲያዊ ባልሆነ አገዛዝ ውስጥ የሚገኝ አንድ ማህበር የፓለቲካ ተፅእኖ የማይደርስባት መሆኑን ፊፋ እንዴት ሊቆጣጠር እና ሊያረጋግጥ ይችላል?

ጉባኤው ሁሉም ማህበራት ለፊፋ ደንብ መገዛት እንዳለበት ወስኗል። ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ ሃገራት ማህበራትን ጨምሮ ማህበራት የራሳቸውን ደንብ የማዋቀር ስራ ሂደትዊ ነው። በእርግጥ ሁሉም እስከሁን በእዚህ ውስጥ አላለፉም።  አንዳንድ ቦታዎች ከሌሎቹ ፈጥነዋል። በአሁኑ ጊዜ ገሚሱ ማህበራት በዚህ ለውጥ ውስጥ አልፈዋል። ነገር ግን ሂደቱ ደረጃ በደረጃ የሚሆን ነው። የፊፋ የስነስርዓት ደንብ በበርካታ ነገሮች ላይ መረጋገጥ አለበት ይኸውም የማህበሩንን የቢሮ የስራ ዘመን የሚመሩትን ለመምረጥ የሚደረገው ሂደት ዲሞክራሲያዊ መንገድ የተከተለ መሆን አለበት።
በፊፋ ጣልቃ ገብነት አማካኝነት ወሳኝ የሚባል መሻሻል ያሳዩ ምሳሌ የሚሆኑ አገራት አሉ?

አዎ ጥቂት ሃገራት አሉ። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜያት የቆየ ችግር ነበር። እናም ለተወሰኑ ጊዜያት ታገዱ። በመጨረሻ ከመንግስት እና ከማህበራት ጋር በጋራ በመሆን ለቀውሱ መፍትሄ አግኝተናል። ከዚያ ወዲህም ከመንግስት ጋር ያለው ግንኙነት በጣም ጥሩ ሆኖ ቆይቷል። እኛም እግርኳሱ እንዲበለፅግ በእጅጉ አግዘናቸዋል።
ሌላው ጉዳይ በብሩኔ ዳሬሰላም የነበረው ነው።በሌላ የእግርኳስ አመራር ቁጥጥር ስር እንዲውል በመፈለጉ ማህበሩ በመንግስት ምዝገባው እንዲነፈገው ተደርጎ ነበር። ይህ ደግሞ [እ.ኤ.አ.] ከመስከረም 2009 እስከ ግንቦት 2011 ድረስ የዘለቀ የእገዳ ቅጣትን አስከትሏል። አሁን ግን ማህበሩ ዳግመኛ ተመዝግቦ መረጋጋት ተፈጥሯል። እኛም በፊፋ ደንብ ቁጥር አንድ ዓላማ መሰረት በጋራ በእግርኳስ ልማት ላይ ትኩረት አያደርገን እንገኛለን። 

Advertisements