ፍላጎት/ እንግሊዛዊው አጥቂ ዳንኤል ስተሪጅ በኢንተር ሚላን ኢላማ ውስጥ ገብቷል

Daniel Sturridge is wanted by Inter

ዳንኤል ስተሪጅ በ2013/2014 የውድድር ዘመን ከቀዮቹ ጋር በግሉ አስደናቂ ጊዜን ቢያሳልፍም ከዚህ አመት በኋላ ግን ጉዳት እና የአቋም መውረድ እንግሊዛዊውን ጥበበኛ ዳግም እንዳያንጸባርቅ አድርጎት በሊቨርፑል ቤት እንዲባክን መንገዱን ከፍቶለታል ፡፡

በያዝነው የውድድር አመት ዳንኤል ስተሪጅ በ15 ጨዋታዎች ላይ ብቻ የተሰለፈ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜም ሊቨርፑል ስፓርታክ ሞስኮን በገጠመበት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ተቀይሮ በመግባት ጨዋታውን ካደረገ በኋላ በጭንቅላት ጉዳት ምክንያት እስካሁን የሊቨርፑልን መለያ መልበስ አልቻልም፡፡

ይህንን የተመለከተው የጣሊያኑ ክለብ ኢንተርሚላንም እንግሊዛዊውን አጥቂ ዳንኤል ስተሪጅን የግሉ ለማድረግ ከወዲሁ ለሊቨርፑል ጥያቄ ለማቅረብ መሰናዳቱን ስካይ ስፖርት ያስነበበ ሲሆን ምን አልባትም የኢንተር ሚላን ጥያቄ ዳንኤል ስተሪጅን ወደ ጁሴፔ ሜዛ እንዲያቀና ሊያደርገው እንደሚችል ጨምሮ ገልፅዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የ28 አመቱ  እንግሊዛዊው አጥቂ ዳንኤል ስተሪጅ ወደ አንዳሉሲያኑ ክለብ ሲቪያ በውሰት እንደሚያቀና በስፋት ቢዘገብም የስፔኑ ክለብ እስካሁን ለቀድሞ የቼልሲ ተጫዋች ይፋዊ ጥያቄ አለማቅረቡን ተከትሎም ኢንተር ሚላን ብቸኛው ፈላጊው ክለብ ሆኗል፡፡

ሆኖም ግን ፍሊፕ ኮቲንሆን በባርሴሎና የተቀሙት ሊቨርፑሎች ዳንኤል ስተሪጅን በጥሩ የዝውውር መስኮት ለሌሎች ክለቦች አሳልፈው መስጠት የማይፈልጉ ሲሆን በተለይም በአውሮፓ ቻምፒየንስሊግ በእንግሊዝ ኤፍ ኤካፕ ዋንጫ እና በፕሪሚየር ሊጉ ላይ በሚኖሩ ጨዋታዎች ላይ ሰፊ ስብስብ ለመያዝ እንግሊዛዊውን አጥቂ ማቆየትን እንደ አማራጭ መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡

Advertisements