ስምምነት / የዛማሌኩ አሊ ጋብር ወደ ዌስትብሮም ለማቅናት ስምምነት ላይ ደረሰ

​የእንግሊዙ ዌስትብሮሚች አልቢዬን ከአህመድ ሄጋዚ በኋላ በድጋሚ እይታውን ወደ ግብፆቹ በማድረግ የዛማሌኩን ተከላካይ አሊ ጋብርን ለማዘዋወር ስምምነት ላይ እንደደረሰ ታዉቋል።

በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ላለመውረድ ከሚታገሉት ውስጥ አንዱ የሆነው ዌስትብሮም ግብፃዊ ተጫዋቾች የተስማሙት ይመስላል።

በቅርቡ በውሰት ከአል አህሊ ወስደውት የነበረው አህመድ ሄጋዚን በቋሚነት ካስፈረሙት በኋላ በድጋሚ እይታቸውን ወደ ግብፅ ፕሪምየርሊግ አድርገዋል።

በተለይ ክለቡ አለን ፓርዲውን ከቀጠረ በኋላ በአህመድ ሄጋዚ እንቅስቃሴ በመማረካቸው ሌላ ግብፃዊ ተጫዋች እንዲያዘዋውሩ በር ከፍቶላቸዋል።

ተረኛው ደግሞ የዛማሌኩ ተከላካይ አሊ ጋብር ሆኗል።ዌስትብሮም ተጫዋቹን እንደ አህመድ ሄጋዚ ሁሉ በመጀመሪያ ዝውውሩን በውሰት ለማድረግ ከዛማሌክ ጋር ተስማምቷል።

ስምምነቱም አወዛጋቢው የዛማሌክ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞርታዳ ማንሱር ጭምር ማረጋጋጫ የተሰጠው ሲሆን ለውሰት ውሉ ዌስትብሮም 500 ሺ ዩሮ ለግብፁ ቡድን ይከፍላል።

ከውሰት ውሉ በኋላ ተጫዋቹን በቋሚነት ለማስፈረም ደግሞ ተጨማሪ 2.5 ሚሊየን ዩሮ ብቻ በመክፈል ዝውውሩን ወደ ቋሚነት መቀየር ይችላል።

በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ መሀመድ ሳላህን ጨምሮ የግብፃዊያን ተጫዋቾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እየመጣ እንዳለ መረዳት ይቻላል።

በ2018 የአለም ዋንጫ ላይም አፍሪካን ከሚወክሉት አገሮች ውስጥ አንዷግብፅ በመሆኗ በአለም ዋንጫው ላይ ተጫዋቾቿ የሚያሳዩት ብቃት ደግሞ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት በተጨማሪ እንዲያቀኑ በር እንደሚከፍትላቸው ይጠበቃል።

Advertisements