ስንብት/ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከአሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ጋር ተለያየ

3.jpg

በፋይሰል ሀይሌ

በ2009 የከፍተኛ ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት በማስመዘገብ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ ችለው የነበሩት አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለብ ጋር በስምምንት ተለያይተዋል፡፡

በፕሪሚር ሊጉ ጅማሮ በአስደናቂ ግስጋሴ ሊጉን በቀዳሚነት ሲመሩ የሰነበቱት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲዎች የኋላ ኋላ በሊጉ በጧላቸው ነጥቦች ምክንያት ወደታች በማሽቆልቆላቸው የክለቡ ደጋፊዎች ተቃውሞዋቸውን ሲገልጹ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ወላይታ ዲቻ በሳምንቱ መጨረሻ በነበረው የሊጉ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላም ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡

አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን እየመሩ በሊጉ እስካሁን 12ጨዋታዎችን አድርገው 2 ጨዋታ አሸንፈው በ7 ጨዋታ አቻ ተለያይተው በ3 ተረትተው 9 ግቦች አስቆጥረው በአንጻሩ 13 ግቦች ተቆጥሮባቸው በ13 ነጥቦች ከወራጅ ቀጠናው በ4 ነጥብ ርቀው በ10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለው ነበር፡፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚያብሄር ምትክም የቡድኑን ምክትል አሰልጣኝ ሀብቶም አብረሀምን በጊዜያዊነት የሾመ ሲሆን በቀጣይም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ አዳማ ከተማ ጋር በሚያደርገው የፕሪሚየር ሊጉ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ሀብቶም አብረሀም ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት እየመራ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

Advertisements