ተጠያቂነት / ኢያን ራይት አሌክሲስ ሳንቼዝ ከአርሰናል ለመውጣቱ ተጠያቂው ማን እንደሆነ አሳወቀ

የቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ኢያን ራይት ቺሊያዊውን አሌክሲስ ሳንቼዝ ወይንም እንደሱ አጠራር የአርሰናል ጀግና ለመሆን አቅም የነበረውን ተጫዋች ከክለቡ ለመውጣቱ ተጠያቂ የሚሆነውን አካል አሳውቋል።

በአርሰናል ከታዩ አጥቂዎች ውስጥ እንደ ትየሪ ኦነሪ ሁሉ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው እንግሊዛዊው ኢያን ራይት በአሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ዩናይትድ ማቅናት በተመለከተ ሀሳቡን ሰጥቷል።

ራይት ለቀድሞ ክለቡ “ለወደፊት ጀግና ለመሆን አቅም የነበረው” እያለ ያሞካሸው አሌክሲስ ሳንቼዝ ከክለቡ መልቀቁ ድጋፍ ቢሰጠውም ተጫዋቹ ከአርሰናል ለመልቀቁ ተጠያቂ ሊሆን የሚችለውን አካል አሳውቋል።

ሳንቼዝ ከጥቂት ቀናት በፊት በቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች በሆነው ማርቲን ኪዎን ዝውውሩን አስመልክቶ ሳንቼዝ በእግርኳስ የታየ “ቅጥረኛ ነፍሰገዳይ”ሲል ጠንካራ ትችት ቢያቀርብበትም ኢያን ራይት ግን በዝውውሩ ብዙ የከፋ ስሜት እንዳልተሰማው ገልፇል።

አያይዞም የክለቡ ቦርድ ብዙ ሊመልሳቸው ያልቻሉ ጥያቄዎች በመኖራቸው ለሳንቼዝ ከክለቡ መልቀቅ ተጠያቂ እንደሆነ ተናግሯል።

“ሳንቼዝ በተለያዩ ጊዜ የሆነ ነገር ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።አሁን የክለቡ ጀግና የመሆን አቅም የነበረው ተጫዋችም ወደ ማንችስተር ዩናይትድ አቅንቷል። ለዚህም ምላሽ ያልሰጠው የክለቡ ቦርድ ተጠያቂ ነው።መልካም እድል ሳንቼዝ፣ለክለቡ ሁሉን ነገር ሰጥተሀል።”በማለት ኢያን ራይት አስተያየቱን አጠቃሏል።

Advertisements