አስደንጋጭ/ አልቫሮ ሞራታ እና ሴስክ ፋብሪጋስ ከካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ውጭ ሆኑ

Chelsea will be without Alvaro Morata and Cesc Fabregas for Tuesday's second leg at Arsenal

4 ክለቦች ብቻ የቀሩበት የካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት አጋማሽ ይደረጋሉ፡፡ ከጨዋታዎቹ መካከልም አርሰናል እና ቼልሲ  የሚያደርጉት ጨዋታ ቀዳሚውን ግምት ያገኘ ሲሆን በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ ላይም ሁለቱ ስፔናዊያን ኮከብች አልቫሮ ሞራታ እና ሴስክ ፋብሪጋስ እንደማይሰለፉ እርግጥ ሆኗል፡፡   

በኤሜሬትስ ስቴዲየም በሚደረገው ፍልምያ ሁለቱ ኮከቦች ከጨዋታው ውጪ መሆናቸውን ጣሊያናዊው የቼልሲ አለቃ አንቶንዮ ኮንቴ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ እንደ አሰልጣኙ ገለፃ ከሆነ አልቫሮ ሞራታ በጀርባ ጉዳት ምክንያት ጨዋታው ያልፈዋል።

ሆኖእም በጉዳት ምክንያት ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጨዋታውን አንድሬስ ክሬስቴንሰን ለዚህ ጨዋታ ሊደርስ እንደሚችል አንቶንዮ ኮንቴ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ዛሬ ምሽት በኤሜሬትስ በሚደረገው ጨዋታ መርታት የቻለው ቡድን በወርሀ የካቲት በዌምብሌይ  ለሚደረገው የካራባኦ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ማለፉን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

Advertisements