የሚኪታሪያን ቁጥር ታወቀ በአውሮፓ ማኅበረሰብ ግን መልበስ አይችልም!

ሚኪታሪያን ቁጥር ታወቀ በአውሮፓ ማኅበረሰብ ግን መልበስ አይችልም!

ዘገባ – በናታ

በሌክስ ሳንቼዝ ልውውጥ ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አርሴናል የተዘዋወረው የ29 ዓመቱ ወጣት አርሜኒያዊው አማካኝ ተጫዋች ሄኒሪክ ሚኪታሪያን በአዲሱ ቡድኑ የሰሜን ለንደኑ ቡድኑ አርሴና ለብሶ የሚጫወተው የመለያ ቁጥር ይፋ ሆነ። ነገርግን ሚኪታሪያን ያንን የመለያ ቁጥር አድርጎ በአውሮፓ ማኅበረሰብ ጫወታዎች ላይ መሳተፍ አይችልም።

ሄኒሪክ ሚኪታሪያን የሚለብሰው 7 ቁጥር መለያን ሲሆን ይህም በቅርቡ አሌክስ ሳንቼዝ ይለብሰው ነበር። 7 ቁጥር መላያን በአርሴናል ቡድን የነበሩት ሮበርት ፔሬዝ፣ ኬቨን ካንቤልና ዴቪድ ሮካስልን የመሳሰሉ ታሪካዊ ተጫዋቾች ለብሰውት መጫወታቸው ይታወሳል።

ሚኪታሪያን 7 ቁጥርን በማኅበረሰቡ ጫወታዎች ላይ መልበስ የማይችለው በአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ሕግ መሰረት በአንድ የውድድር ዓመት አንድ ቁጥር ከአንድ ተጫዋች በላይ መልበስን ይከለክላል። 7 ቁጥርን መለያ አርሴናል ከኮለን ጋር ባደረጉት ጫወታ ላይ አሌክስ ሳንቼዝ ለብሶ በመጫወቱ እገዳው ይጸናል።

ምንጭ – ጎል ስፖርት።wp-1516649964714.jpeg

Advertisements