የዕለተ ማክሰኞ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች

የእንግሊዝ ጋዞጦቹ በዕለቱ ይዘዋቸው የወጡ አበይት የጥር ወር የዝውውር ወሬዎች 

the sun

 • ማንችስተር ሲቲ አይመሪክ ላፓርቴን የፈለገ ሲሆን የአትሌቲክ ቢልባዎን ኮከብ የውል ማፍረሻ 60 ሚ.ፓውንድ ለመክፈልም እያጤነበት ይገኛል።
 • ሳውዛምተኖች ካደረጓቸው 15 የሊግ ጨዋታዎች መካከል አንዱን ብቻ ማሸነፍ የቻሉትን ማውሪሲዮ ፔሌግሪኖን የማሰናበት ውሳኔ ላይ የሚደርሱ ከሆነ የቀድሞውን የዋትፎርድ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫን ምትክ አድርገው ለመቅጠር የሚያጤኑባት ይሆናል።
 • ላዛና ዲያራ በአስገራሚ ሁኔታ ወደፒኤስጂ ለመዛወር ተቃርቧል።
 • የሻምፒዮንሺፕ ክለቦቹ ሊድስና ሚልዎል የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ሲሉ የአስቶንቪለውን የመኃል ተከላካይ ቶሚ ኢልፊክን ለማዛወር ፈልገዋል።

daily mirror

 • ቼልሲ ኤዲን ጄኮን እና ኤመርሰን ፓልሜሪን ከሮማ በ50 ሚ.ፓውንድ ለማዛወር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
 • ቦሩሲያ ዶርትሙንዶች ኦሊቪየ ዥሩ የፒየር-ኤመሪክ አውባምያንግ የዝውውር ለውጥ አካል እንዲሆንላቸው ወይም ዝውውሩ እስከመጪው ክረምት ድረስ እንዲቆይ ጠይቀዋል።
 • ኦክስፎርድ ዩናይትዶች ሰኞ ዕለት ያሰናበቷቸውን አሰልጣኙ  ፔፕ ኮልቴት ምትክ ይሆናቸው ዘንድ ፊታቸውን ወደቀድሞው የቼልሲ ተጫዋች ፍረንክ ላምፓርድ ሊያዞሩ ይችላሉ።
 • ዌስት ሃም ዩናይትዶች በጉዳት ምክኒያት አንዲ ካሮል ለሶስት ወራት እና ማኑኤል ላንዚኒ ለስድስት ሰምንታት ከሜዳ እንደሚርቁ በመረዳታቸው ሃቪየር ኸርናንዴዝ በጥር ወር ክለቡም እንዲለቅ አይፈቅዱለትም።
 • ኢስላም ሲሊማኒ ወደቤሽኪታሽ መሄድ የመቻሉ ጉዳይ ክላውድ ፑየል ሁለት አጥቂዎችን ለማጠት የማይፈልጉ በመሆናቸው ሌላኛው አጥቂ ኡሉዋ በሌስተር ይቆያል።
 • ቻርልተን አትሌቲኮች በሊቨርፑል እና ኤቨርተን የሚፈለገውን ለእንግሊዝ ከ20 ዓመት በታች የሚጫወተውን ተከላካይ፣ ኢዝሪ ኮንሳን በ5 ሚ.ፓ ለመሸጥ ተስማምተዋል።
 • ማይክል ኦኔል በስኮትላንድ እግርኳስ ማህበር የስንብት ዕጣ ከገጠማችው በኋላ አሌክስ ማክሊሽ ወደስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን የአሰልጠኝነት ሚና የመመለስ ፍላጎት አላቸው።

daily express

 • ኒውካሰል ዩናይትዶች የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ኬቨን ጋሜሮን ወደሴንት ጀምስ ፓርክ ለማምጣት በሚችሉበት የስምምነት ጉዳይ ላይ ንቁ እንቅስቀሴ እያደረጉ ይገኛሉ።
 • አርስናል እና ቶተንሃም የፒኤስጂውን የክንፍ ተጫዋች ሉካስ ሞራን በ35 ሚ.ፓ ለማስፈረም ከትናንት ምሽት ጀምሮ ከፍተኛ ፉክክር ይዘዋል።
 • ቼልሲዎች ኤዲን ጄኮን ወደፕሪሚየር ሊጉ ለመመለስ በዓመት 7 ሚ.ፓ ማግኘት የሚቻበት የኮንትራት ስምምነት አቅርበውለታል።
 • የኒውካሰሉ አማካኝ ጆንጆ ሼልቪ በ12 ሚ.ፓ. ወደዌስትሃም ለመዛወር ተቃርቧል።
 • ሙሳ ዴምቤሌ በዚህ ወር ሶቲክን ለመልቀቅ ወደውጭ እየማተር ነው።

daily telegraph

 • የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት በአውሮፓ እግርኳስ ላይ እየተንሰራፋ በመጠው የበዛ የክፍያ መጠን እና የወኪሎችን የክፍያ ጣራ ላይ ጥብቅ ገደብ የማበጀት ጉዳይ ማህበሩ ምክክር ማድረግ እንደሚጀምር ገልፀዋል።

the guardian

 • ዌስት ሃሞች አጥቂያቸው አንዲ ካሮል በእግሩ ላይ በገጠመው ጉዳት የቀዶ ህክምና ከተረገለት በኋላ ለሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ገልፀዋል።
 • ሌሎች አራት የቀድሞ የቼልሲ የወጣቶች ማሰልጠኛ ተጫዋቾች በክለቡ የወጣቶች ማሰልጠኛ አሰልጠኞቹ ግራሃም ሪክስ እና ግዋይን ዊሊያምስ ደረሰብን ባሉት የዘረኝነት ጥቃት በክለቡ ላይ ክስ ሊመሰርቱ ነው።

daily star

 • የሮማ የእግርኳስ ፋይሬክተር የሆኑት ሞንቺ ኤዲን ጄኮን የሚሸጡ ከሆነ ሊቨርፑሉን ለመልቀቅ የተቃረበውን ዳንኤል ስተሪጅን በዝውውር ዝርዝረቸው ውስጥ ሊያስገቡት እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
 • ዎልቭሶች የቦርንማውዙን አጥቂ ቤኒክ አፎቤን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር ከዌስት ብሮም ጋር ተቀላቅለዋል።
 • ዌስት ብሮሞች ጆኒ ኢቫንስን በዚህ ወር የማይሸጡት ከሆነ የዋትፎርዱን አጥቂ ትሮይ ዴኒን የማስፈረም ጥረታቸውን የሚያዘገዩት ይሆናል።

daily mail

 • ኒውካሰሎች የቼልሲውን የክንፍ ተጫዋች ኬኔዲን በ24 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ በውሰት ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ነው።
 • ኤሪክ ዳየር ቶተንሃሞች የዓለም የዝውውር ክብረወሰን በሆነ ዋጋ እንኳ ቢሆን ላለመሸጥ ያደረጉትን ቁርጠኝነት አድንቋል።
 • ክሪስታል ፓላሶች የዛግሌቢ ሉቢኑን ተከላካይ ጃሮስላው ጃክን በ2 ሚ.ፓ ለማስፈረም ተቃርበዋል።
Advertisements