ይፋዊ / ጆሴ ሞሪንሆ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ተፈራረሙ

ማንችስተር ዩናይትድ ​ጆሴ ሞሪንሆ ከክለቡ ጋር ያላቸው ኮንትራት ማራዘማቸው ይፋ አደረገ።

 በመጀመሪያ አመት ቆይታቸው የዩሮፓ ሊግ እና የሊግ ካፕ ዋንጫን በማንሳት በዩናይትድ የአሰልጣኝነት ታሪክ በመጀመሪያ አመት የተሻለ ቆይታ ያደረጉት ጆሴ ሞሪንሆ ለተጨማሪ አመታት ከክለቡ ጋር መቆየታቸው እርግጥ ሆኗል።

ጆሴ ከዩናይትድ ጋር በኮንትራት ማራዘሚያ ዙሪያ ድርድር እያደረጉ እንደነበር ሲነገር የቆየ ሲሆን በአዲሱ ስምምነታቸውም ቢያንስ እስከ 2020 ድረስ የሚቆዩ ይሆናል።

ስለ ስምምነቱ የተናገሩት ኤድ ውድዋርድ “ጆሴ ከወዲሁ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስምምነት አድርጓል።ቢያንስ እስከ 2020 ድረስ ኮንትራታቸውን ስላደሱ ደስተኛ ነኝ።ለስራው ያለው ትጋት እና አክብሮት የተለየ ነው።” በማለት ለክለቡ እና ከደጋፊው ውጤት እንደሚያመጡ ተናግረዋል።

ጆሴ በበኩላቸው “የዩናይትድ አሰልጣኝ በመሆኔ የእውነት ኩራት ይሰማኛል።ለባለቤቶቹ እና ለኤዲ ውድዋርድ በስራዬ እውቅና ስለሰጡኝ ትልቅ ምስጋና አቀርባለው።ለዚህ ትልቅ ክለብ የሚሆን ትክክለኛ አሰልጣኝ እንደሆንኩ ስላመኑብኝ ደስተኛ ነኝ።

“በአንድ አመት ሶሰት ዋንጫዎችን ለማግኘት ትልቅ እቅድ አቅደናል።ቡድኔም እንዲያቅደው የምፈልገው ነው።ለወደፊቱ ውጤታማ የሆነ ማንችስተር ዩናይትድን ለመገንባት እቅድ አለን።” በማለት ደጋፊዎችን ተጫዋቾችን ጨምሮ አመስግነዋል።

Advertisements