ማንችስተር ሲቲ በክለቡ ክብረ ወሰን ዋጋ የላ ሊጋውን ኮከብ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል

​በጥሩ የዝውውር መስኮት በሁለት ትልልቅ ዝውውሮች በተቀናቃኞቹ  የተሸነፈው ማንችስተር ሲቲ ለበርካታ ጊዜያት ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየውን የአትሌቲኮ ቢልባኦ ተከላካይ አይምሪክ ላፖርቴ ለማዘዋወር ከጫፍ መድረሱን ማርካ ዘግቧል፡፡

እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ሁለቱ ክለቦች ለክለቡ ሪከርድ በሆነ 57 ሚልዮን ፓውንድ ዋጋ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የህክምና ምርመራውንም በባስክ ማጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡

ተጫዋቹ ትናንት ክለቡ ቢልባኦ ከአይባር ጋር በነበረበት የላ ሊጋ ጨዋታ ከክለቡ ጋር ያልነበረ ሲሆን የዝውውሩን መቃረብ ተከትሎ ራሱን እንዲያዘጋጅ ከክለቡ ፈቃድ እንደተሰጠው ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡

በፕሪምየር ሊጉ አናት ላይ ተመቻችቶ የተቀመጠው ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ ቨርጂል ቫንዳይክንና አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት ተጫዋቾቹን በሊቨርፑልና በማንችስተር ዩናይትድ መነጠቁን ተከትሎ ባይሳካም በቀጣዩ ሰኞ ወይም ማክሰኞ ላፖርቴን አስፈርሞ የተከላካይ መስመሩን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል፡፡

Advertisements