ቶተንሀሞች አሰልጣኛቸው ማውሪሲዬ ፖቸቲኖን በማድሪድ እንዳይነጠቁ ከፊታቸው ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ተገለፀ

ማድሪዶች የቶተንሀም አሰልጣኝ የሆነው ማውሪስዬ ፖቸቲኖን የዚዳን ተተኪ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ከባድ ፈተና እንደተጋረጠበት ታውቋል።

ማድሪዶች ባለፉት አመታት ያሳዩ የነበረው ጠንካራ አቋማቸው አሽቆልቁሎ ከወዲሁ ከላሊጋ እና ከኮፓ ዴልሬ በጊዜ በመውጣታቸው በአሰልጣኙ ዜነዲን ዚዳን ቆይታንን ጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቶታል።

ዚዳን በሁለት ተከታታይ የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን በማንሳት ጣፋጭ ሁለት የውድድር አመታታትን አሳልፏል።የ 2016/2017 የስፔን ላሊጋንም ከባላንጣው ባርሴሎና ቀድሞ በማሸነፍ በማድሪድ ቤት ሲሞካሽ ቆይቷል።

ነገርግን ማድሪድ እንዳለፉት አመታት የተደላደለ የውጤት ጉዞን ማድረግ ባለመቻላቸው ከሁለት ውድድሮች በጊዜ መውጣት ችለዋል።

በተለይም በሳምንቱ አጋማሽ በኮፓ ዴልሬ በሌጋንስ ያጋጠማቸው አስደንጋጭ ሽንፈት የዚነዲን ዚዳን ቀጣይ ቆይታ ላይ ቆም ተብሎ እንዲታሰብበት አድርጓል።

ዚዳን በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ውስጥ ወደ አሸናፊነቱ የማይመለስ ከሆነ ከሀላፊነቱ የመነሳት እድሉ የሚሰፋ ሲሆን በምትኩ ደግሞ የስፐርሱ ማውሪሲዬ ፓቸቲኖ መታጨታቸው ታውቋል።

አንዳንድ ዘገባዎችም ማድሪዶች ከወዲሁ ከፓቸቲኖ ጋር ግኑኝነት ማድረግ መጀመራቸውን የገለፁ ሲሆን አሰልጣኙም የሰጡት አስተያየት ምናልባትም የዚዳን ተተኪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ፍንጭ የሰጠ ነበር።

“በእግርኳስ የሚሆነውን ነገር አታውቀውም።በዚህ ሙያ ውስጥ የተረጋጋ ነገር የለም፣ችግሩ ይህ ነው።”ሲሉ ፓቸቲኖ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Advertisements