ሽኝት / አርሰናል ለኦሊቬ ዢሩ ዝውውር የሚፈልገውን ያህል ሂሳብ ከቀረበለት አጥቂውን ለከተማው ተቀናቃኝ ለመስጠት መዘጋጀቱ ተነገረ

አርሰናል የከተማው ተቀናቃኙ የሆነው ቼልሲ 35 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ ከሆነ ኦሊቬ ዢሩን አሳልፎ ለመስጠት መዘጋጀቱ ተነገረ። 

ዴይሊ ሜይልን ጠቅሶ ቴሌግራፍ እንደፃፈው ከሆነ የሰሜን ለንደኑ ክለብ በር በሩን እያየ የሚመለከተውን የ 31 አመቱን ፈረንሳዊ አጥቂ ለመሸጥ መዘጋጀቱ የታወቀ ሲሆን የኦቦምያንግ ዝውውር ለመጠናቀቅ መቃረቡም የዢሩን ስንብት እንደሚያፋጥነው ታውቋል። 

​ዢሩ ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ወደ ሰሜን ለንደን የሚመጣ ከሆነ ይበልጥ ከተሰላፊነት እንደሚርቅ እሙን ሲሆን በመጪው የሩሲያ አለም ዋንጫ በሀገሩ ፈረንሳይ ስብስብ ውስጥ የመካተቱ ነገርም አስጊ ነው።  

ከዚህ ጋር በተያያዘም ዢሩ የመድፈኞቹ አራተኛ ተመራጭ ተሰላፊ ከመሆን ይልቅ ወደሌሎች ክለቦች ለማምራት እንደሚፈልግ እየተጠቀሰ ይገኛል። 

ዶርትሙንድም ፈረንሳዊውን አጥቂ በውሰት ወደጀርመን በመውሰድ ለኦቦምያም በጊዜያዊ ምትክነት ሊጠቀምበት ጥያቄ ማቅረቡ በስፋት ተነግሯል። 

ነገርግን ዢሩድ ወደ ዶርትሙንድ የማምራት ፍላጎት ይኑረው አይኑረው ገና አልተረጋገጠም። 

Advertisements