ኤፍ ኤ ካፕ/ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ቀጣይ የጨዋታ ድልድል ይፋ ሆነ

የታሪካዊውና የጥንታዊው የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ዋንጫ (ኤፍ ኤ ካፕ) አምስተኛ ዙር ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

በድልድሉም መሰረት የፕሪምየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ከ ሻምፒዮንሺፑ መሪ ዊጋን ጋር የተደለደለ ሲሆን ሌላኛው የማንችስተር ከተማ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ከሃድርስፊልድና በርሚንግሃም አሸናፊ ጋር ከሜዳው ውጪ እንዲጫወት ተደልድሏል፡፡
በባለፈው አመት ውድድር ፍፃሜ ደርሶ በአርሰናል ተሸንፎ ዋንጫ ያጣው የምህራብ ለንደኑ ቼልሲ በበኩሉ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሃል ሲቲን እንዲያስተናግድ መርሃ ግብር ወጥቶለታል፡፡

በዝቅተኛ ዲቪዚዮን ከሚጫወተው ኒውፖርት ካንትሪ ጋር ተጫውቶ ለጥቂት ከመሸነፍ የተረፈው ቶተንሐም ሆትስፐር የመልሱን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ከሚልዎልና ሮችዴል አሸናፊ ጋር የሚፋለም ይሆናል፡፡

ሌስተር ሲቲ በሜዳው ኪንግ ፓወር ከሼፍልድ ዩናይትድ የሚጫወት ሲሆን ዌስትብሮም በበኩሉ ከፕሪምየር ሊጉ ሳውዛምፕተን ጋር ተደልድሏል ፤ ብራይተን በበኩሉ ኮቨንትሪ ሲቲን በሜዳው እንዲያስተናግድ መርሃ ግብር ወጥቶለታል፡፡

የኤፍ ኤ ካፑ አምስተኛ ዙር ጨዋታዎች በቀጣዩ የካቲት ወር አጋማሽ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

Advertisements