ዳኒ አልቬዝ ኔይማር ከባርሴሎና የለቀቀበትን ምክንያት አሳወቀ

ብራዚላዊው ዳኒ አልቪዝ የቡድን አጋሩ እና የሀገሩ ልጅ የሆነው ኔይማር ጁኒየር ከባርሴሎና ለምን እንደለቀቀ ከፊፋ ድረገፅ ገር ባደረገው ቆይታ ላይ ተናግሯል።

ከሲቪያ ወደ ባርሴሎና ከተዛወረ በኋላ በስኬት የተሽቆጠቆጡ ጊዚያትን ከካታላኑ ክለብ ጋር ማሳለፍ የቻለው ብራዚላዊው ደኒ አልቬዝ ከኔይማር ጋር በፓሪስ ሴንት ጄርሜይ እየተጫወቱ ይገኛሉ።

የቀኝ ተከላካዩ አልቬዝ ከፊፋ ድረገፅ ጋር በነበረው ቆይታ ምላሽ ከሰጠባቸው ነጥቦች ውስጥ ኔይማር ባርሴሎናን ለምን ለመልቀቅ እንደወሰነ ይገኝበታል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በአለም የዝውውር ሪከርድ ወደ ፓሪሱ ክለብ ያቀናው ኔይማር ለምን ባርሴሎናን እንደለቀቀ የተለያዩ ሀሳቦች ሲሰጡ ቆይቷል።

የአንዳንዶቹ ተጫዋቹ የሚያገኘው ዳጎስ ያለ ክፍያ ሳያማልለው እንዳልቀረ በመጥቀስ ተጫዋቹ ለገንዘብ ሲል ወደ ፓሪስ እንዳቀና ሲናገሩ

በሌላ ወገን ደግሞ የአንድ ቡድን አውራ ሆኖ ለመታየት እና ከሜሲ ሽፋን ለመላቀቅ እንደሆነ የጠቀሱ ነበሩ።

የቡድን አጋሩ የሆነው ዳኒ አልቬዝም በሁለተኛው ምክንያት ይስማማል። ተጫዋቹ ባርሴሎናን የለቀቀው ከሜሲ ጥላ ስር ለመላቀቅ እንደሆነ ከፊፋ ድረገፅ ጋር በነበረው ቆይታ አሳውቋል።

ኔይማር ከፔዤ ጋር ለቀጣዮቹ አመታት የመቆየቱ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ በድጋሚ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ስፔን ተመልሶ ለሪያል ማድሪድ ሊፈርም እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

ከሰሞኑን የወጡት መረጃዎችም ተጫዋቹ ለፔዤ የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ማስገኘት የሚችል ከሆነ ወደ ሪያልማድሪድ እንዲያቀና ፈቃድ እንደሚሰጠው ነው።

Advertisements