የተረጋገጠ/ ማንችስተር ሲቲ በክለቡ ክብረወሰን ዋጋ ፈረንሳያዊውን ኮከብ አስፈረመ

​ፕሪምየር ሊጉን በ 12 ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ የተከላካይ መስመሩን እጅግ ሊያጠናክርበት ይችላል በተባለለት ዝውውር ፈረንሳያዊውን የመሃል ተከላካይ በክለቡ ሪከርድ ዋጋ ከወደስፔን አስመጥቷል፡፡

<!–more–>

የፔፕ ጓርዲዮላውን ስብስብ የተቀላቀለው የአትሌቲኮ ቢልባኦ የመሃል ተከላካይ አይምሪክ ላፖርቴ በኢትሃድ ለአምስት አመታት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን ለዝውውሩ ፈሰስ የተደረገበት 57 ሚልዮን ፓውንድ በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው የዝውውር ሒሳብ ሆኗል፡፡

አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ የተጫዋቹን ዝውውር ተከትሎ በአፋጣኝ ወደጨዋታ እንደሚያመጣው በሰጠበት አስተያየት ” አዎ! ጨዋታዎችን ያደርግ ስለነበር ወደሜዳ ለመግባት ዝግጁ ነው ፤ በርግጥ ፕሪምየር ሊጉ በብዙ መንገዶች የተለየ ነው፡፡ ሊጉ ለወጣቶች አስቸጋሪ ቢሆንም በጊዜ ቆይታ ይላመደዋል ” ብሏል፡፡

ላፖርቴ ከ 18 ወራት በፊት ከማንችስተር ሲቲ ቀርቦለት የነበረውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

Advertisements