ስኬት / ሜሶት ኦዚል በክለቡ የክብረ ወሰን ሰባሪ የደሞዝ ክፍያ በአርሰናል ለመቆየት ተስማማ


ሜሶት ኦዚል ለተጨማሪ ሶስት አመታት በአርሰናል ለመቆየት ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናትም ፊርማውን ያኖራል።

ኦዚል ለወራት ሲያወዛግብ የነበረውን የአርሰናል ቤት ቆይታውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሚቋጭ መልኩ የክለቡ ትልቁ ተከፋይ የሚያደርገውን የ 350,000 ፓውንድ ስምምነት ላይ ደርሷል። 

አርሰናል ከጀርመናዊው ጨዋታ አቀጣጣይ በተጨማሪ የጃክ ዊልሻየርን የውል ስምምነት ለማራዘም ከስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቡን ተከትሎ ሌላኛው የክለቡ አወዛጋቢ የዝውውር ሂደት በቀጣይ ጊዜ እንደሚጠናቀቅ እየተገለፀ ይገኛል።  

ዊልሻየር እንደ ቡድን አጋሩ ኦዚል የኢምሬትስ የውል ስምምነቱ በመጪው ክረምት የሚጠናቀቅ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደረጉ ያሉ ድርድሮችም ከጫፍ እንደሚደርሱ ከፍተኛ ምልክቶች እየታዩ ይገኛል። 

ኦዚል በዚህ የጥር የዝውውር መስኮት ከፕሪምየር ሊጉ ውጪ ካሉ ክለቦች ጋር ንግግር የማድረግ መብት እና በመጪው ክረምትም በቦስማን ህግ መሰረት አርሰናልን የመልቀቅ እድል ነበረው። 

ነገርግን የኢምሬትሱ ክለብ ትልቅ ጥረት በማድረግ ኢዚል በእዛው ህልሙን ማሳካት እንደሚችል በመግለፅ የ 29 አመቱን ተጫዋች ማሳመን የቻለ ሲሆን በዝውውር ላይ ያደረገው ተሳትፎም ኦዚልን በኢምሬትስ በማቆየት ረገድ መጠነኛ እገዛን አድርጎለታል። 

በዚህ በያዝነው የጥር የዝውውር መስኮት አሌክሲስ ሳንቼዝን ማጣት ለአርሰናል ትልቅ ጉዳት ቢሆንም የሄነሪክ ማኪቴሪያን እና የፒየር ኤምሪክ ኦቦምያንግ ለክለቡ መፈረም ኦዚል በኢምሬትስ እንዲቆይ በመጠኑ እንዳነሳሳው ይታመናል።  

አርሰናል ጉዳዩን በማስመልከት በሰጠው መግለጫም ኦዚል ገና የውል ስምምነት ፊርማውን አለማኖሩን ነገርግን በቅርቡ ሁሉም ነገር እንደሚጠናቀቅ እና ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል። 

Advertisements