ሽንፈት / የሪያድ ማህሬዝ የሲቲ ዝውውር ሳይሳካ ቀረ

የሌስተር ሲቲው የክንፍ ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ የማምራት ነገር ሳይሳካ ቀርቷል። 

የኢትሀዱ ክለብ አልጄሪያዊውን ተጫዋች በተመለከተ እስካሁን ድረስ አንድም ይፋዊ ጥያቄ ያላቀረበ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም በውስጥ ለውስጥ ድርድሮችን ከክለቡ ሌስተር ጋር ሲያደርግ መሰንበቱ ተጠቁሟል።

ሌስተር ዛሬ ረፋድ ላይ ለክንፍ ተጫዋቹ 95 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲከፈለው እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሲሆን ሲቲ በበኩሉ ለተጫዋቹ የመጨረሻ ብሎ የመደበው ሂሳብ 60 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑ ለዝውውሩ አለመሳካት በእንቅፋትነት ተጠቅሷል። 

ሲቲ ለረጅም ጊዜ ሲያድነው የቆየውን ሳንቼዝን ባለማግኘቱ ማህሬዝ የተፈለገው ለቺሊያዊው አጥቂ ምትክነት እንዲሁም ደግሞ በጉዳት ላይ የሚገኘውን የሊሮይ ሳኔ ቦታ እንዲሸፍን ታስቦ ነበር። 

Advertisements