ኦዝል ኮንትራቱን አራዘመ!

ኦዝል ኮንትራቱን አራዘመ!

ዘገባ – በናታ።

ጀርመናዊው የአርሴናል አማካኝ ተጫዋች መሱት ኦዝል አሌክስ ሳንቼዝን ተከትሎ አርሴናልን ይለቃሉ ከሚባሉት ተቻዋቾች ዝርዝር ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ሲጠራ ከነበሩት የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ተርታ በቀዳሚነት ሲጠራ መቆየቱ ይታወሳል። የውል ስምምነቱ ሊጠናቀቅ የስድስት ወራት ውል ብቻ የቀረው መሱት ኦዝል በይፋ አርሰናልን እንደማይለቅ ዛሬ በፊርማው አረጋግጧል።

ኦ

 

የ29 ዓመቱ ወጣት ጥበበኛው ኦዝል ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ተኩል የአርሴናል ተጫዋች ሆኖ ይቀጥላል። ይህም 32 ዓመት እስኪሞላው ድረስ እስከ 2021 እ.ኤ.አ. በአርሴናል ይቆያል። ኦዝል በሳምንት 350,000 ፓውንድ ተከፋይ ይሆናል። ይህም የአርሴናል ከፍተኛው ተከፋይ ያደርገዋል።

ኦዝል ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ በ2013 እ.ኤ.አ. በአርሴናል ክብረወሰን በ42.4 ሚሊዮን ፓውንድ መፈረሙ ይታወሳል። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ21 ጫወታዎች ላይ ተሰልፎ 4 ጎል ያገባ ሲሆን 6 ለጎል አመቻቶ አቀብሏል።

 

ምንጭ – ቢቢሲ ስፖርት።

 

Advertisements