የተረጋገጠ/ ቶተንሐም ሆትስፐር ሉካስ ሞራን ከፒ ኤስ ጂ አስፈረመ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሐም ሆትስፐር ብራዚላዊውን የፓሪስ ሴንት ጀርሜይን የመስመር አማካይ ሉካስ ሞራን አስፈርሟል፡፡

የጥሩ የዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን በበርካታ ትልልቅ ዝውውሮች ታጅቦ ሊጠናቀቅ የተቃረበ ሲሆን የፕሪምየር ሊጉ ክለቦችም በርካታ ሚሊዮኖችን ፈሰስ በማድረግ በዝውውሩ ላይ በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ክለቡ የ25 አመቱን አማካይ ለማስፈረም 25 ሚልዮን ፓውንድ ፈሰስ ያደረገ ሲሆን ከአምስት አመታት የፈረንሳይ ቆይታው በኋላ የሞሪሲዮ ፖቼቲኖን ስብስብ ተቀላቅሏል፡፡

ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን 36 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው አማካይ ዶሮዎቹን ከተቀላቀለ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ከጎኔ በመሆን እዚህ እንድገኝ የረዱኝን በሙሉ አመሰግናለሁ ፤ ይህ የኔ አዲስ ምህራፍ ጅማሮ ነው፡፡በአዳዲሶቹ የቡድን ጓደኞቼ ደስተኛ ነኝ፡፡እዚህ ብዙ ድንቅ ጊዜ ይጠብቀኛል ምክንያቱም ስብስባችን በጥራትና በችሎታ የተሞላ ነው ” ብሏል፡፡

አማካዩ በፓሪሱ ክለብ በነበረው ቆይታ 229 ጨዋታዎችን በክለቡ መለያ ያከናወነ ሲሆን 46 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል፡፡

Advertisements