የተረጋገጠ/አርሰናል በክለቡ ክብረ ወሰን ዋጋ አውባሚያንግን አስፈረመ

የሰሜን ለንደኑ አርሰናል የክለቡ ክብረወሰን በሆነ 56 ሚልዮን ፓውንድ ዋጋ ጋቦናዊውን አጥቂ ፔር-ኤምሪክ አውባሚያንግን ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ አስፈረመ፡፡

አውባሚየንግ በመድፈኞቹ ቤት ለሶስት አመታት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን በጀርመኑ ዶርትሙንድ የአራት አመት ተኩል ስኬታማ ቆይታን ካደረገ በኋላ አሌክሲስ ሳንቼዝ ትቶ የሄደውን ክፍተት ለመሸፈን ወደአርሰናል መጥቷል፡፡

ክለቡ ለተጫዋቹ ሳምንታዊ የ180 ሺህ ፓውንድ ክፍያ እንደሚሰጠው የተነገረ ሲሆን የሱን እግር ተከትሎ የፈረንሳያዊው አጥቂ ኦሊቬ ጂሩ ቆይታ በቋፍ ላይ ይገኛል፡፡

ጋቦናዊው በቀድሞ ክለቡ በ 213 ጨዋታዎች 172 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሁነኛ የጎል ሰው ሲሆን የአገሩ የምንጊዜውም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው ፤ በተጨማሪም የ2015 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ በመመረጥ ብቸኛው ጋቦናዊ መሆን ችሏል፡፡

Advertisements