የተረጋገጠ / ኦሊቬ ዢሩ ወደቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቀቀ

 

ኦሊቬ ዢሩ ወደቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር በ 17.5 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ በማጠናቀቅ በስታምፎርድ ብሪጁ ክለብ የ 18 ወራት የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

ፈረንሳዊው አጥቂ በአዲሱ ክለቡ 18 ቁጥር መለያን እንደሚለብስ የሚጠበቅ ሲሆን የእሱን ዝውውር መጠናቀቅ ተከትሎም ሚቹ ባትሱሀይ ወደ ዶርትሙንድ በውሰት መሄዱ ይፋ እንደሚሆን እየተገለፀ ይገኛል። 

ቼልሲ 30 አመት ላለፈው ተጫዋች ረጅም የውል ስምምነት ወይም የውል ማራዘሚያ ስምምነት ያለማቅረብ ጥብቅ ፖሊሲ ቢኖረውም የ 31 አመቱ ዢሩ የክለቡን አሰራር ማስቀየር ችሏል። 

የስታምፎርድ ብሪጁ ክለብ ከሰሞኑ ከፒተር ክሮች ጀምሮ ስሙ ከአጥቂዎች ማስፈረም ጋር ሲያያዝ የቆየ ሲሆን የፈረንሳዊው አጥቂ ወደክለቡ መምጣትም በውድድር ዘመኑ ቀሪ ቆይታ ላይ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል። 

Advertisements