ክለብ አልባ የነበረው የቀድሞው የአርሰናል ኮከብ በመጨረሻም ለጣሊያኑ ክለብ ፈረመ

ከስድስት ወራት በላይ ክለብ አልባ ሆኖ ቆይቶ የነበረው የቀድሞ የአርሰናል ድንቅ ተጫዋች ላለመውረድ እየታገለ ለሚገኘው እና በጣሊያን ሴሪ ኣ የመጨረሻ ደረጃ ለያዘው ቡድን ፊርማውን አኖረ።

ፈረንሳዊው ባካሪ ሳኛ ከመድፈኞቹ ጋር የነበረው ድንቅ ቆይታ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ማንችስተር ሲቲ በማቅናት መጫወት ችሏል።

ተጫዋቹ ከሲቲ ጋር ባለፈው ክረምት ከተለያየ በኋላ ክለብ አልባ የነበረ ሲሆን በመጨረሻ ማረፊያው ለጣሊያኑ ቤኒቬንቶ አድርጓል።

ሳኛ እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ በሴሪኣው ላለመውረድ ለሚጫወተው ክለብ የሚቆይ ሲሆን ለተጨማሪ አመትም ከክለቡ ለመቆት በውሉ ላይ እንደ አማራጭ ተቀምጧል።

ተጫዋቹ ሰባት ነጥብ ብቻ ለያዘው ቤኒቬንቶ መፈረሙ ብዙዎቹ ያልጠበቁት ቢሆንም እሱ ግን በትክክለኛው ወቅት ትክክለኛውን ክለብ መቀላቀሉን አሳውቋል።

በ2018 የአለም ዋንጫ ላይም የፈረንሳይ ብሔራዊ  ቡድን ወክሎ መሳተፍ እንደሚፈልግ ጨምሮ ተናግሯል።

60 ጨዋታዎችን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ሳኛ በፕሪምየርሊጉ ላይ ለአርሰናል እና ለሲቲ ከ 260 ጨዋታዎች በላይ መሳተፍ ችሏል።

Advertisements