በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ አምስቱ ፈጣን ጎሎች ውስጥ ክርስትያን ኤሪክሰን ማንችስተር ዩናይትድ ላይ ያስቆጠራት ጎል አንዷ ሆናለች።የእስከዛሬዎቹ ፈጣን ጎሎችስ የትኞቹ ናቸው?
ቶተንሀም ሆትስፐር ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ 2-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ተጫዋቹ በ 11ኛው ሰከንድ ላይ ማስቆጠር ችሏል።
ኤሪክሰን ያስቆጠራት ጎልም የፕሪምየርሊጉ ከተቆጠሩ ፈጣን ጎልች ውስጥ አንዷ ሆና ተመዝግባለች።
ለመሆኑ በፕሪምየርሊጉ ፈጣን ጎሎች ተብለው የተመዘገቡ አምስት ጎሎች እነማን ያስቆጠሯቸው ናቸው?
5 – ድዋይት ዮርክ (13 ሰከንድ)
ኮቨንትሪ 0-3 አስቶን ቪላ (ቅዳሜ,መስከረም 30, 1995)
የቀድሞ የዩናይትድ እና የቪላ ተጫዋች የነበረው ዮርክ 1995 ላይ ኮቨንትሪ ላይ ለማስቆጠር ያስፈለገው 13 ሰከንድ ብቻ ነበር።ይህም ፈጣን ጎል በፕሪምየርሊጉ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
4 – ማርክ ቪዱካ (11 ሰከንድ)
ቪዱካ አለን ስሚዝ ያመቻቸለትን ኳስ ቻርልተን ላይ ወደ ጎል የቀየራት ፈጣን ጎል አራተኛ ደረጃን ይዛለች።
3 – ክርስቲያን ኤሪክሰን (11 ሰከንድ)
ቶተንሀም 2-0 ዩናይትድ(እሮብ,ጥር 31, 2018)
ኤሪክሰን የዩናይትድ ተከላካዮች ትኩረት ማነስ ተከትሎ በዴቪድ ዲሂያ መረብ ላይ ማስቆጠር ችሏል።
2 – አለን ሺረር (10 ሰከንድ)
ኒውካስትል 2-0 ማን ሲቲ (ቅዳሜ,ጥር 18, 2003):
ለኒውካስትል ሲጫወት የነበረው ሺረር 2003 ላይ የሲቲ ግብጠባቂ ካርሎ ናሽ ስህተትን ተጠቅሞ ያስቆጠራት ጎል በሁለተኛነት ተቀምጧል።
1 – ሌድሊ ኪንግ (10 ሰከንድ)
ብራድፎርድ 3-3 ቶተንሀም (ቅዳሜ,ታህሳስ 9, 2000)
የቀድሞ የስፐርሶች ተከላካይ የነበረው እንግሊዛዊው ሌድሊ ኪንግ በ 2000 ላይ ቫሊ ፓሬድ ላይ ከርቀት ያስቆጠራት ጎል የፕሪሚየርሊጉ ፈጣኗ ጎል በመባል ሪከርዱን ይዟል።