አሳዛኝ / ስዋንሲ ሲቲ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በጉዳት ምክንያት ሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ማሰልፍ እንደማይችል ማረጋገጫ ሰጠ

ስዋንሲ ሲቲ ሊሮይ ፌር እና ዊልፍሬድ ቦኒ በደረሰባቸው ጉዳት የተነሳ ቀሪው የውድድር ዘመን እንደሚያልፋቸው ማረጋገጫ ሰጥቷል። 

ካርሎስ ካርቫሀል የደቡብ ዌልሱን ክለብ ከያዙ ጀምሮ ቡድኑን ከወራጅ ቀጠና ለማውጣት በብርቱ እየሰሩ ቢገኝም ትናንት ምሽት ቡድኑ ከሌስተር ጋር 1-1 አቻ በተለያየበት ጨዋታ የቡድኑ አማካኝ ፌር በደረሰበት የቋንጃ ጉዳት ቀዶ ጥገና ሲያስፈልገው ቦኒም በተመሳሳይ በጅማት መበጠስ ቀዶ ጥገና ማድረግ አስፈልጎታል። 

ክለቡ የሁለቱን ተጫዋቾች ጉዳት በማስመልከት ባወጣው መግለጫም ሆላንዳዊው የመሀል ሜዳ ሞተር እና አይቮሪኮስታዊው አጥቂ በተደረገላቸው ምርመራ ጉዳታቸው ከፍተኛ እና ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው መሆኑ በመታወቁ የውድድር በቀሪው የውድድር ዘመን ወደሜዳ እንደማይገቡ ተገልጿል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ወሳኝ ሚና ለቡድኑ እየተወጣ የነበረው ፌር በአዲሱ ፈራሚው አንዲ ኪንግ እንደሚተካ ሲጠበቅ የአንድሬ አየው ወደቡድኑ ዳግም መምጣት እና የታሚ አብረሀም መኖር ስዋንሲ በፊት መስመር ላይ አማራጭ እንደሚኖረው ተወስቷል።

Advertisements