“ሀዛርድ የባለንዶር አሸናፊ ይሆናል” – ሴስክ ፋብሬጋዝ

ኤደን ሀዛርድ የባለንዶር አሸናፊ የመሆን ምልክቶች እና ብቃቶች እንዳሉት የቡድን አጋሩ ሴስክ ፋብሬጋዝ ተናግሯል። 

ሀዛርድ ባሳለፍነው ዓመት የውድድር ዘመን በቼልሲ የፕሪምየር ሊግ ስኬት ላይ ቁልፍ ሚና የነበረው ቢሆንም በግላዊ ክብር ደረጃ አሸናፊው የሆነው የክለብ አጋሩ ኒጎሉ ካንቴ ሲሆን ቤልጄማዊው ኮከብ በባለንዶር ሽልማት ትልቅ ስኬቱም በ 2015 ስምንተኛ ደረጃን ያገኘበት ነው።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስምንት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ሀዛርድ ባሳለፍነው ዓመት ማሳየት የቻለውን አይነት ብቃት በቋሚነት ማሳየት ባይችልም ፋብሬጋዝ ከስካይ ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ የቡድን አጋሩ በአለም እግር ኳስ ላይ ምርጥ የሚባል ብቃት ያለው ተጫዋች እንደሆነ በመግለፅ አድናቆቱን ገልጿል። 

ፋብሬጋዝ ሲናገርም “እሱ አንድ ለአንድ ከተቃራኒ ተጫዋች ጋር ሲገናኝ ትልቅ ብቃት ማሳየት የሚችል ነው። ኳስ መያዝ፣ ማቀበል እና ከኳስ ጋር አስደናቂ ብቃት ማሳየት የሚችል ነው። ሀዛርድ ባለንዶርን ማሸነፍ ከፈለገ ሁሉ ነገር በእሱ የሚወሰን ነው። 

“እኔ ለብዙ ጊዜያት ከትልልቅ ተጫዋቾች ጋር ተጫውቻለሁ። እሱ ምርጥ ተጫዋች ነው። እሱ ማድረግ የሚችለውን አውቃለሁ። ለእሱም ነግሬዋለሁ። በእኔ አስተያየት ባለንዶርን የማሸነፍ ብቃት አለው።  …” ብሏል።

Advertisements